ቤተክርስቲያናችን

ቤተክርስቲያናችን እንዳትናድ አባቶቻችን አንድ እንዲሆኑና በአንድ ሲኖዶስ እንድንመራ
============================================================
ቤተክርስቲያናችን እንዳትናድ አባቶቻችን አንድ እንዲሆኑና በአንድ ሲኖዶስ እንድንመራ
============================================================
ክርስትና እንዳይስፋፋ ለ300 ዓመታት ያህል ንጉስ ቁስጠንጢኖስ ክርስትና ህጋዊ ሃይማኖት እንዲሆንና ክርስቲያኖችም በነጻነት እንዲያመልኩ እስካወጅበት ድረስ ክርስቲያኖች ሁሉ ህይወታቸውን ለክርስቶስ ፍቅር በመሰዋት የሰማእትነትን ከብር ተቀዳጅተው ነበር። ከዚያ በሁዋላ ግን ለሃይማኖት በመሞት የሚገኘው ሰማዕትነት ሲያበቃ ክርስቲያኖች የጌታችን ኢየሱስን ፈለግ ለመከተል ሰማእት ለመሆን በፈቃደኝነት እራሳቸውን በማደህየት ፡ የዚህ ዓለምን ገንዘብና ምቾት ሳይሆን መላ ሕይወታቸውን ለሞተላቸው የፍቀር ለአምላክ ሰጥተው ለእምነታቸው ጽናት ለቤተክርስቲያናችው ዕድገትና ጥንካሬ መኖር በመምረጥ በተናጠል በበረሃ ተለይተው በጾምና በጸሎት በመንፈሳዊ ህይወት የሚኖሩት መጠሪያ “መነኩሴ” ይባላሉ። እንዱሁ ክርስቲያን የሆንን ሁሉ በገንዘብና ጥቀም ሳንሸነፍ ለክርስትና ህይወታችን መስዋዕትነትና ክርስቲያናዊ ህይወትን እንድንኖር የነሱን አርዓያ ለመከተል መጣርን በማመልከት የመነኩሴ ጾምና በጸሎት ከአምላክ አስታራቂ እንደሚሆን ለኛም የመነኩሴ ጸሎትና ልመና አስታራቂ መንፈስን እንድንዲልክልንና በእንድ እንድንነሳሳ መነኩሴ ተብሎ ተሰይሟል።
በእንግሊዝኛ አገላለጹ _MENEKUSE/monk or nun is an individual who is totally dedicated his or her lives to GOD, taken the vows of poverty, chastity and obedience, serve the church in special way, work for salvation of the world, and strive for the perfection of charity in His/Her own lives. MENEKUSE is an outstanding sign of the Church and a witness of Jesus Christ
የድህረ ገጹ መጀመሪያ ፎቶግራፍ ምንድነው???
በድህረገጹ ያለው ፎቶግራፍ በእርግጥ ምንድነው የሚያሰኝ ነው። ማወቁ ደግሞ መንፈስን የሚፈውስ የክርስትና አውታራችን ነው። ፎቶግራፉ ከላይ የተነሳና ከመላው ዓለም የተሰበሰቡ ክርስቲያኖች ዙሪያውን ከበው ለመዳሰስ የሚታገሉበት በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ጎልጎታ ውስጥ የሚገኘው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከሲኦል ለማውጣት ተወግሮ ተሰቅሎ ተቀብሮ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት የመቃብሩ ቦታ ነው ። ከፓትርያርክ እስከ ተራ ምዕመን ያለነው የክርስቶስ ተከታይ ስለሆንን የጌታችንን ኢየሱስ ፍቅር ሰላም እያሰብን ቂምን ትተን ፍቅርን፡ ጠብን ትተን ሰላምን ለማምጣት ለእምነታችን እንድንቆም ድህረገጹን በከፈትን ቁጥር ለፍቅሩ እንድንገዛ ለማሳሰብ ነው።
የድህረ ገጹ አዘጋጆች እነማን ናቸው? በቤተክርስቲያናችን ከምንሰማውና በግል ንባብ ካገኝነው ዕውቀት ሌላ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ትምህርት የሌለን ተራ ምዕመናን ስንሆን በቤተክርስቲያናችን ላይ የምናየው ሁኔታን ስላሳዘነን ያቅማችንን ለማበርከት የተነሳን ተራ ምዕመናን ነን።
If you are a professional please join us to help something in some way.
God Bless You All.
Melekuse TeamM
Info@melekuse.org
የመለኩሴ ዌብ ሳይት ዋና ዓላማ፤ ቤተክርስትያናችንን፣ገዳማትን፣ ሃይማኖታችንን(ኦርቶዶክስ ተዋህዶ)፣አባቶችን እና አገልጋዮችን በሃሳብም ሆነ በቁሳቁስ መርዳትና መደገፍ ነው።
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
gallery_20141205_1267047732.jpg
http://melekuse.org/images/joomgallery/details/gallery_2/angeles__8/gallery_20141205_1267047732.jpg
gallery_20141205_1805249207.jpg
http://melekuse.org/images/joomgallery/details/gallery_2/angeles__8/gallery_20141205_1805249207.jpg
gallery_20141205_1890281965.jpg
http://melekuse.org/images/joomgallery/details/gallery_2/church-_4/gallery_20141205_1890281965.jpg
first_category_9_20140903_1263888101.jpg
28.jpg
http://melekuse.org/images/joomgallery/details/gallery_2/jesus____5/28.jpg
page1-img1.jpg
blog-img3.jpg
page1-img2.jpg
slide-3.jpg
blog-img5.jpg