በቀረው ዓለም

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፡ በቀረው ዓለም ሃገሮች

ጥንት ለትምህርት ይላኩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ቢለመኑ እንኩዋን በውጭ ሳይቀሩ ወደሃገራቸው እምቢ ብለው ይመለሱ የነበረበው ሂደት፣ በሃገር ተከብሮ

በሰላም የመስራት ፡ የመኖር ዋስትናና ፡ የሃገር ፍቅር ፡ ተንዶ  ችግርና ረሃብ በመንገሱ፣ ላለፉት 45 ዓመታት ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም ተሰደዋል።  ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሆነ

ሁሉ ለሁለት ሺሀ ዓመታት በመላው ዓለም የተበተኑ እስረኤላውያን በሄዱበት ሁሉ በንግድ ፡በትምህርት በመጎልበት ፣ ዕውቀትና ንብረት በማፍራት ከምድረ ገጽ ጠፍታ የነበረችውን

እስራኤል እንደገና ከ1878 ዓመታት በሁዋላ በዓለም ካርታ ላይ ያልነበረች በቃልኪዳን ስምዋ እስራኤልን በ1948 እንደወለዷት ሁሉ፣ በመላው ዓለም የተበተኑ ኢትዮጵያንም 

ከስታ የጠቋቆረችውን ኢትዮጵያም እንድታብብና መልካም ፍሬ እንድታፈራ  አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

 ኢትዮጵያዊ ባለበት ቦታ ሁሉ የእኔነት መገለጫቸው የሆኑ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ፣ የሃገር ልብስ፣  የሃበሻ  ምግብ ቤቶች ሱቆችና ቤተክርስቲያናትም አብረው ተሰደው

ይገኛሉ።፣ ዛሬ  የኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሌለበት ታላላቅ የዓለም ከተማ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። በውጭ ዓለም ያሉ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ቤተክርስቲያንን እንቅስቃሴ  ስንመለከት፦ 

  •  የምዕራቡ ክፍል አማኝና አምልኮተ እግዚአብሄር የሚፈጽም  በመጥፋቱ፡ ቤተክርስቲያናት ወደ ንግድ ቤት እየተለወጡ ሲዘጉ፣ ብዙዎቹን እየገዛን  አዲሶችም  እየተገነቡ ናቸው።

  • ∙ በራስዋ ልዩ ስርዓት የሚቀርበው ቅዳሴ  በመላው ዓለም እየፈሰሰ ፣ ታቦት በፖሊስ ሞተር  ታጅቦ በታላላቅ የአሜሪካና አውሮፓ  ሃገሮች  የጥምቀትና የመስቀል  በዓል

  • እየተከበረ ይገኛል።

  •  ትክክለኛው አምላክ ለሙሴና አሮን ባዘዘው ክብር  የሚፈጸም  አምልኮተ እግዚአብሄር ነው  እያሉ  የሊሎች ዜጎች እየተጠመቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት

    ተከታይ እየሆኑ ናቸው።

  •  ምዕመናን በኦርቶዶክሳዊ ስርዓት  ቅዳሴን ለመከታተል ፣ የሚወለዱ ህጻናት ጥምቀት ለማግኘት ፣ ወጣቶች በቁርባንና በተክሊል ጋብቻቸውን እንዲፈጽሙና ፣ የሞት

  • ስርዓት በወግ ማከናወን፣ ችለዋል

  •    እዚህ አገር የተወለዱ ህጻናት ግዕዙን እያንበለበሉ የሚቀድሱ ካህናት ፣ ዲያቆናትና ፣  ዘማርያንና የሌሊት ሰዓታት ሳይቆር የሚቆሙ ተረካቢ ትውልድ አፍርተዋል

  •  በየጊዜው ከኢትዮጵያ የሚመጡ ጳጳሳት ፣ ካህናትና ግለሰቦች በችግር ላይ ላሉ ገዳማትና ቤተ ክርስቲያናት እርዳታ ሲጠይቁ የማይደርቁ ምንጮች በመሆን የዶላር

  •  ችቦ አስይዘው ይልካሉ

  •  በሃገራችን ኢትዮጵያ የረሃብና የተለያዩ ችግሮች ሲደርሱ በምሕላ ጸሎት በማድረስ ፣ ካ ላቸው ገንዘብ በመቀንስና ምዕመናን በማስተባበር የሚያደርጉት እርዳታ

  • ኦሮቶዶክሳዊነት መለምለሙን ያሳያል።

                                                                                            

 በመላው ዓለም እድገትዋ ሲያስደስት ከእርሱ ጋር ግን ፈጽሞ ያልተጠበቁ ለቤተክርስቲያናችን ህልውና  ፈታኝ የሚሆኑ በብልሃት መወገድ ያለባቸው  ችግሮችም አልጠፉም።

  •  ከሃገር ባስወጣን  እልህ ፡በጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን  ፍቅር መሰረት ባለመቻቻል ካህናትና ምዕመናን ቡድን ለይተው ቤተክርስቲያን ከቀኖና ውጭ

  • በየቦታው መክፈት፣

  •  እንደመንፈሳዊ  በሰላም  በመጨረስ ፋንታ  በማያምኑ ፍርድ ቤት በመካሰስ ከምዕመናን የተሰብሰበ ገንዘብ ለጠበቃ ሲሳይ መዳረግ ለቤተክርስቲያን እንቅፋት

  • ተፈጥሯል (የተካሰሱ ቤተክርስቲያናትና ያወጡት ወጭ  ወደፊት በጥናት ማቅረብ ለእርምት ይረዳል)

  •  ሰው ከአምላኩጋር በፍቅር ለመነጋገር፡ ሰላም ለማግኘት የሚሄድባትን ቦታ በሚያዪት ጠብ  በአካባቢው ላለመድረስ ዕርም በቤቴ እጸልያለሁ እያሉ  ምዕመናን

  • እንዲቀሩና  ወደሌላ ቤተክርስቲያንና እምነት  እንዲሄዱ ማድረግ ፣

  •  በውጭ ተወልደው ቤተክርስቲያን በመምጣት ላይ ያሉ ልጆች ትላንት አባቶች ብለው  የሚያከብሯቸው ፥ በማግስቱ በሚያዩት ጸብ  እየተደናገሩ ከቤተክርስቲያን

  • እንዲርቁና  ተረካቢ አልባ ማድረግ  ፣                                                                                                                                                   

ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ለቤተክርስቲያን ታላቅ አደጋ ስለሆኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከፈለንን በፍቅር በመመራት በትልቅ ራዕይ በመተባበር፣  ብዙ ምዕመን የሌላቸው

የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች በማእከላዊነት  በተጠናከረ መልክ ተደራጅተው ትንንሽ የግል ቤተክርስቲያን ከመክፈት ይልቅ አማኝ እያጡ የሚዘጉ ታላላቅ የካቶሊክና

የሌሎች  ቤተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን በህብረት ገዝተው  ( https://abbey.suscopts.org/ ፣   https://www.stmaryatlanta.org/  በአሜሪካና አውርፓ

ብቻ ሳይወሰኑ ታላቅ የየአህጉራት  ጳጳሳት በመመደብ  እኛ ያልደረስንባቸው  ጎረቤቶቻችን ሳይቀር  በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ  የተራድኦ ስራዎቻቸው ኬኛ ፣ ታንዛንያ ፣ ዩጋንዳ፣ 

ናይጂሪያ  ፣ ዛምቢያ ፣ ዝምባብዌ ፣ ዛየር ፣ ናምቢያና ደቡብ አፍሪካ የሚያከናውኑት ተግባር ያስገርማል። 

 

 እኛም በቀና ክርስቲያናዊ እሳቤ በሃገራችን ኢትዮጵያ ፣ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳለኢምና በመላው ዓለም ያሉንን  ቤተክርስቲያናችንና ወገኖችንን ለማገዝ ይህን የመነኩሴ ድህረ ገጽ   www.menekuse.org  ቀርቧል። ድህረ ገጹ በመነኩሴ ተብሎ  የተሰየመበትም ዓላማ ፡ መነኩሴ ከዓለም እራሱን ገድሎ ለእግዚአብሄር ባሪያ ለመሆን ቆርጦ በገዳም

ተለይቶ በጸሎትና ትህትና ተወስኖ የአምላክ ባሪያ እንደሆነ ሁሉ  እኛ በዓለም የምንኖረውም እንደ መነኩሴ ሆነን በመንፈሳዊ ተግባር  ቤተክርስቲያናችን   እንድናሳድግ 

ሁሉም እንዲሳተፍ  የመነኩሴ ድህረ ገጽ  አዘጋጆች በታላቅ መንፈሳዊ ትህትና እናሳስባለን።

abu