በኢየሩሳሌም ታላቁ የደብረገነት ኪዳነ ምህረት ገዳም

 

የደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ገዳም በ1874ዓ ም ተመስርቶ / በኢየሩሳሌም ከተማ የሚገኝ/

 

ከታች በፎቶግራፉ የሚታየው የደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ወብ ገዳም ፡ በአጼ ዮሐንስ ተጀምሮ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ የተጠናቀቀ ፡ የጥንት አባቶቻችን ያሰሩት ቅርስ ሲሆን ይህንን ቅርሳችንን ተንከባክበን አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ይሆናል፡፡

በዚህ ገዳም ብዙ መነኮሳት አባቶችና እናቶች  የሚኖሩበት መኖሪያ ቤቶች ፡ አዳራሽና ፡ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ተያይዘውም የሚከራዩ ቤቶች ያሉት ታላቅ የቤተክርስቲያንዋና የሃገር ኩራት የሆነ ቅርስ ሲሆን ብዙ መሻሻል፡መሰራትና መጠበቅ ያለባቸው ስራዎች አሉ። ገዳሙን በጠቅላላ ለማሳደስ ምን እንደሚፈልግ  የምህንድስናና ሌሎች ዘርፍ ባለሙያዎች ፤ የገንዘብና የሁሉንም ዕውቀት ፡ ድጋፍና እንክብካቤ በመፈለጉ በአሁኑ ጊዜ ዋናው ቤተመቅደስ እድሳቱ የተጠናቀቀ ሲሆን በዙሪያው ብዙ መሰራት ያልባቸውን ስራዎች እየተከታተሉ የገዳሙን አገልግሎት ማሳደግ የሚችሉ ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል። 46

4

 

 ዴር ሱልጣን መድሃኔዓለምና ቅዱስ ሚካኤል ገዳማት/ 320 ዓ. ም /ጎልጎታ ውስጥ የሚገኝ/

 

ንግስት እሌኒ ልጇ ንጉስ ቁስጠንጢኖስ አሽንፎ ክርስትናን በ313 ዓመተ ምህረት ህጋዊ እምነት ካደረገ በሁዋላ፡ ለአምላክ በገባቸው ቃል ኪዳን መሰረት በሁሉም መንፈሳዊ ቦታዎች ገዳማትንና መቅደሶች አሰርታለች። ካስገነባቻቸው ገዳማት ዋናው ጊታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጎልጎታ ውስጥ  ያሰራቸው ባለ ብዙ መቅደሶች  ሲሆን ኢትዮጵያውያንም በዚያ በመኖራቸው አራት መቅደሶችን ለኢትዮጵያውያን ስጥታን ለረጅም ዓመታት ስንገለገልባቸው ከቆየን በሁዋላ የኢትዮጵያ መንግስት በዘመነ መሳፍንት ተዳክሞ መነኮሳቱ የሚያገኙት የድጋፍ ግንኙነት በመቋረጡ መዳከማቸውን ተገን አድርገው በጎልጎታ ውስጥ የነበሩንን መቅደሶቻችንን  ብንነጠቅም ፤ መነኮሳቱ ከዚያ ለቀው ላለመሄድ ባደረጉት ቁርጠኛ ተጋድሎ የተውሰኑ ቦታዎችን  በመያዝ እስከዛሬም ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በአስቃቂ ሁኔታ በመኖር በጎልጎታ ያለንን የዴር ሱልጣን መድሃኔዓለምና ተያይዞ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል መቅደሶች ይዘን አለን ። 

 

የዴርስ ሡልጣንን  ገዳም በሚመለከት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጽህፈት ቤት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር  2000  ዓ ም ያዘጋጀው ጸሁፍ ፡ የገዳሙን ታሪኩንና ችግሩን ያካተተ በመሆኑ ጽሁፉን እንዳለ ኢትዮጵያውንን ለማሳወቅ ሰለሚረዳ ከዘህ በታች ሙሉው ጽሁፍ እንዳለ ለንባብ ቀርቧል።ከታች የተመለከተው ፎቶ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋናው ጎልጎታ መቃብር ጋር ር ተያይዞ  የሚገኘው የዴር  ሡልጣን መድሃኔዓለም የኢትዮጵያ ገዳም ሲሆን ምዕመናንም በላይኛው የገዳሙ መግቢያ በር ገብተው ከውስጥ በደረጃ ወርዶ ተያይዞ በሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ገዳም በር በመውጣት ወደ ዋናው ጎልጎታ ይገባል። እስካሁንም የማንኛውም አገር ጎብኚ በመቅደሳችን ውስጥ እያለፈ ወደዋናው ጎልጎታ ይገባል።

 

ይህ የዴር ሱልጣን መድሃኔዓለም ገዳም የውስጡ ገጽታ ሲሆን የውጭውን ገጽታዎች  ፎቶዎች ከጽሁፉ መጨረሻ ተያይዘዋል

 

 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የኢየሩሳሌም ገዳማት በ2000 ዓመት ምህረት የቀረበው ሙሉ ጽሑፍ ከታች ቀርቧል

 

“ዴር ሡልጣን ፡ ሥያሜው በግዕዝ ደብረ ሥልጣን ፥ በዓረብኛ ሡልጣን ሲሆን ይህ ገዳም የሚገኘው ከጌታ ቅዱስ መቃብር ቤተመቀደስ በስተምስራቅ ከቅድስት ዕሌኒ ቤተመቅደስ በላይ ነው።ዴር ሡልጣን ማለት “የንጉሥ/የመሪ/ገዳም” ማለት ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ትርጓሜ ሥያሜውን ያገኘው ቦታው ጥንቱንም ንጉስ ሰሎሞን ከኢትዮጵያ ለበዓላት ለሚመጡ መንገደኞችና መልዕክተኞች ማረፊያ እንዲሆን ለንግስት ሳባ የሰጣት በመሆኑና ኋላም በክርስትናው ዘመን ገዳም ተመሥርቶበት በኢትዮጵያውን ነገስታት ሲረዳ የኖረ መሆኑ ነው።

 

 1. መሰረታዊ ታሪክ ፦

የኢትዮጵያውያንና የቅድስት ሀገር ትውውቅ እስከ ብሉይ ኪዳን ይዘልቃል።

 1. ከክርስቶስ ልደት በፊት ዝነኛው የንግሥተ ሳባና የንጉስ ሰሎሞን የኢየሩሳሌም ግንኝነት ነው /1ኛ ነገ 10፡1-13

 2. በሐዲስ ኪዳን ያለው ትውውቅ የመጀመሪያው ደግሞ ከጌታ ልደት በኋላ ትንቢተ ኢሳይያስን እያነበበ  በሠረገላው ሲጓዝ ቅዱስ ፊልጶስ በመንፈስ ተልኮ ያስተማረውና ያጠመቀው ኢትዮጵያዊ ጃንደርባ ታሪክ ነው። / የሐዋ ሥ ም 8፡26-40/

 3. በ380 ዓ ም ሁለቱ የቅዱስ ጀሮም ደቀመዛሙርት ቅድስት ፓውላና ልጇ ቅድስት ኢዮስቶም  ሮም ለሚገኙት ሊይታና ማርሴላ ለተባሉት ጓደኞቻቸው ወደ ኢየሩዳሌም መጥታችሁ ኑሩ በማለት በላቲን በጻፉት ሁለት ደብዳቤዎች ላይ በየቀኑ መነኮሳ,ት በቡድን ከህንድ፡ ከፋርስና ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩዳሌም እንደሚደርሱ አመልክተዋል። /ደብዳቤችን መፈለግና ማቅረብ/

 4. በ636 ዓ ም ከሊፋ ዑመር ኢብን ኧልኸታብ  ኢየሩሳሌምን ከተቆጣጠረ በኋላ ለክርስቲያኖች ,በሰጠው ቃልኪዳን (ኦማራይት ኮብናንት) ላይ “ በኢየሩሳሌም ውስጥ ከሚኖሩት ሌሎች ክርስቲያኖችም ማለት ጆርዳናውያን፡ኢትዮጵያውያን(ሀበሾች) እንዲሁም ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም(ለመጎብኘት) የሚመጡ እውሮፓውያን ኮፕቶች (ግብጻውያን)፡ አሶራውያን (ኩርዶች)” የሚለው ንባብ የኢትዮጵያውያን ማህበር ከሌሎች ለመሳለም ከሚመጡት አንጻር እንደ ነዋሪ እንደሚታዩ ያረጋግጣል።

 

በኋላ ዘመንም ቢሆን የኢትዮጵያውያንና የቅድስት አገርን ግንኙነት በተለይም ደግሞ  የያዟቸውን ይዞታዎች በትክክል የሚያሳዩ መረጃዎች በብዙ ተሳላሚዎች ጽሁፍ በነገስታት አዋጆችና ሌሎች እንደ ሽሪዓ ፍርድ ቤት ድንጋጌዎች ባሉት ውስጥ ይገኛል።

 1. በ786 ዓ ም ዊልባልድ የተባለ ጅርመናዊ ጳጳስ በገሊላ አንድ ኢትዮጵያዊ ተሳላሚ እንዳገኘ አመልክቷል።

 2. በ1323 ዓ ም ሁለቱ ፍራንሲስካን መነኮሳት ሲሞና ኹጎ የኢትዮጵያውያንን የቅዳሴ ሥርዓት እንደተሳተፉ ሲገልጹ ይህ ዓይነት ቅዳሴ በጎልጎታ ውስጥ በምትገኘው የቅድስት ማርያም ቤተመቅደስና  በቅዱስ ሚካኤል መቅደስ የሚካኬድ እንደሆነ እንዲሁም በ1374 ዓ ም ሂኮሎ ዳ ፖጌቦንሲ የተባለ አባት ገልጻል።

 3. ከ27 ዓመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም የመጣው ሊዎናርዶ ፍሪስኮባልዲ ኢትዮጵያውያን አራት መቅደሶች እንዳሏቸውና ከእነዚህም አንዱ የቅዱስ ሚካኤል መቀደስ መሆኑን ሲገልጽ ሌሎች መንገደኞች ለምሳሌ እንደጀርመናዊው ሲባልድ ሬይተርና ጅሃን ተኑድ ያሉት ይኸንኑ ደግመው አረጋግጠዋል።

 4. በ1517 ዓ ም በሡልጣን ሳሌም በተሰጠ አዋጅና በ1550 በንጉስ ሱልጣን ሱሌይማን የጸናው የኢትዮጵያውያንን ይዞታ የሚዘረዝር አዋጅ ላይ ስለዴር ሡልጣን እንዲህ ተጽፏል።” በስተደቡብ በኩል የሚከፈተው ታችኛው የኢትዮጵያውያን ቤተመቅደስና በመካነ  መቃብሩ ቤተክርስቲያን የሚገባው የሡልጣን ገዳም (ዴር ሱልጣን ከነቤቶቹና ከነመኖሪያዎቹ የኢትዮጵያውያን ንብረት ነው።”

 5. በተጨማሪም በ1530 ዓ ም ፈረንሳዊ ተሳላሚ ዴንስ ፖስት “ አብረሃም ልጁን ይስሃቅን በሰዋበት ቦታ ሀበሾች የሚባሉት ጥቁር ህዝቦች ቤተመቅደስ ይጠብቃሉ፣ በተጨማሪም አብረሃም ልጁን ሲሰዋ ያምር እንደነበር የሚያምር የወይራ እንጨት አለበት፡” በማለት ከነትውፍታዊ መረጃው አረጋግጧል።

 6. ከዚህ ሌላ  ፍራንሲስኮ  ቨርኔሮ በ17ኛው መቶ  ክፍለ ዘመን “ እነርሱ (ኢትዮጵያውያን) ክጌታ ቅዱስ መቃብር ቤት መቅደስ አደባባይ ፊት ለፊት ቤተመቅደስ አላቸው። በዚያም ጥቂት ጠበብ ያሉ ጨለማ ክፍሎች አሉ። በዚያው ባዶ መሬት ላይ ይተኛሉ” ሲል በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በዴር ሱልጣን ያሳለፉትን የተጎሳቆለ ኑሮ አስቀምጧል።

 7. የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት የተከበረ ማህበር እንደነበራቸው ብዙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

 8. በ1531 ና በ1547 ሁለት የኢየሩሳሌም የሸሪዐ ካውንስል ድንጋጌዎች የሚያሳዩት የኢትዮጵያውያን ማህበር እለቃ ከጥንት ጀምሮ ከግሪክ ፓትርያርክ ሳይቀር ቀድሞ የቅዳሜ ሥዑር ዕለት ከጌታ መቃብር /ጎልጎታ/ ውስጥ ብርሃን ያወጣ እንደነበር ሲያረጋግጥ ፣

 9. በሌላ በኩል የኢትዮጵያ  ነገስታት ለምሳሌ አጼ ዐግብዐጽዮን በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እና  አጼ ዘርአያዕቆብ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ መነኮሳት የጻፏቸው ደብዳቤዎች የኢትዮጵያውያን ማህበር ከነገስታቱ በቂ ድጋፍ ይደረግላቸው የነበረ መሆኑን ያሳያል።

ይሁን እንጂ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የግራኝ መሐመድ መነሳትና በኋላም የዘመነ መሳፍንት መከሰት ምክንያት ግንኙነቱ በመቋረጡ አንዳንዶቹ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ወደ አውሮፓ ለመሰደድ በቅተዋል። ችግሩን ችለው የታሪክና የቅድስና ቦታቸውን ለመጠበቅ በኢየሩሳሌም የቀሩትም በጎልጎታ ውስጥ ያላቸውን መብት በግፍ በመነጠቃቸው በዴር ሡልጣን ከመወሰናቸውም ሌላ ከላይ ፍራንሲስኮ ቭርኖሮ ለገለጸው ዓይነት መራራ  ኑሮ ተዳርገዋል። ይሁን እንጂ ዘመነ መሳፍንት አክትሞ  ዘመነ ነገስታት ሲተካ  ለማህበሩ የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል።

 1.   መላ ያጣው ክርክር፡

  1.   በ1774  ዓ ም የኢትዮጵያ  መነኮሳት ኢብራሂም ጁሃሪ የተባለውን ግብጻዊ ከአገልጋዮቹ ጋር በእንግድነት ያስጠጉታል። ውሎ አድሮ  አለቃ  ልሁን ማለት ይገምራል።

  2.   ይሁን እንጂ እንደ ጳጳስ ሳሙኤል ጎባትና የብሪታንያ ቆንስል ጀምስ ፊን ኮፕቶች በዴር ሡልጣን ላይ ግልጽ የይገባኛል ክርክር ያነሱት በገዳሙ በ1838 ዓ ም ከተከሰተ የተስቦ ወረርሽኝ በኋላ ነው።በዚህ ወረርሽኝ የኢትዮጵያ መነኮሳት በተስቦ ሲያልቁ ኮፕቶች በአርመን  ጳጳስ እርዳታ የዴር ሡልጣንንና የሁለቱን ቤተመቅደሶች ቁልፍ ከተረፉት መነሎሳት እጅ በጉልበት ይነጥቃሉ። ከዚያም በኋላ በማጽዳት ስም ቦታውን ለማቃጠል እንዲፈቀድላቸው  በወቅቱ የኢየሩሳሌም አስተዳዳሪ ክነበረው ግብጻዊ ኢብራሂም ፓሻ ይጠይቃሉ ። በአጋጠማቸው ዕድል ተጠቅመው የኢትዮጵያውያንን ትልቅ ቤተመጻሕፍት ያቃጥላሉ።

  3.   ከዚህ በኋላ  በባይዛንታይን ዘመን በአብርሃም ገዳም ምክንያት የተነሳውን ክርክር ይዘው ይገባናል በማለት ጥያቄ  ያቀርባሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩት ቱርኮች  በአብርሃም ገዳምና በዴር ሡልጣን መካከል ልዩ ነት እንዳለ አስረድተው በ1846 ዓ ም እምቢ ይሏቸዋል። ቢሆንም ግን በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉት ድርጊቶች የቱር`ክ አስተዳደር ለግብጾች ማድላቱን የተለያዩ  መረጃዎች አመልክተዋል።

  4.   በ1850 በሳሙኤል ጎባት ምክር የኢትዮጵያውያን የዴር  ሡልጣንን ቁልፍ መልሰው እጅ አደረጉ። በመቀጠል በ1890 ዓ ም ኮፕቶች የሰሚኑን ግድግዳ ለማፍረስ ፈልገው ኢትዮጵያውያኑ መነሎሳት አምርረው በመቃወማቸው የቱርክ መንግስት በይርጋ ደንብ መሰረት አግዷቸዋል።

  5.   በዚህም ንዴት የሁለቱን መቅደሶች ቁልፎች ለውጠው ዘጉ። እስከ 1870?ዓ ም ለኢትዮጵያውያን ዝግ ሆነው በቆየበትም ወቅት ኢትዮጵያውያን የትንሣኤን በዓል በድንኳን ለማክበር ተገደዱ። ሆኖም አጼ ሚኒልክ በደጃዝማች መሸሻ መሪነት የላኩት የልዑካን ቡድን በሰበሰበው መረጃና  ኋላም በተገኙት መረጃዎች መሰረት ለጆርዳን መንግስት አቤቱታ ቀርቦ ክ8 ዓመት ጥናት በኋላ በ1881 የጆርዳን መንግስት ለኢትዮጵያን ወሰነ። በውሳኔው መሰረት ኢትዮጵያውን መነኮሳት ለ40 ቀን ብቻ ቁልፉን ከያዙ በኋላ በግብጽ መንግስት ጣልቃ ገብነት ውሳኔው ተቀልብሶ ኮፕቶች መረጃ ያቀርባሉ በሚል ሰበብ ቁልፉን እንዲመልሱ ተደረገ።ነገር ግን የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡም ሆን ተጨማሪ መረጃ እንዲያቀርቡ ዕድል ሳይሰጣቸው እስከ 1871 ዓ ም ድረስ ጉዳዩ  ተዘግቶ ቆየ።

  6. በ1971 ዓ ም የእስራኤል የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደገና አይቶት ችግሩ እስኪፈታ ድረስ አሁን ባለው መልኩ ኢትዮጵያውያን ገዳሙን እንዲያስተዳድሩ ሲል ወሰነ።ኢትዮጵያውያውያንም የቤተመቅደሶቹን ቁልፎች እጅ እደረጉ።

 2. ኢሰብዓዊነት

ሰብዕና  ትርጉም የሚኖረው ሰው በዓይኑ አይቶ መፍረድ እስከቻለ ድረስ ብቻ ነው። ይህንን ለማለት ያስገደደን ደግሞ በእሁን ሰዓት በገዳሙ ውስጥ ያለው ሁኔታ ነው።

 1.     ከሁለቱ መቅደሶች አንዱ መቅደስ በጣም ትልቅ አደጋ ላይ ያለና  አስቸኳይ ጥገና  የሚያሰፈልገው መሆኑን ማንም በዚያ ያለፈ  ሰው ሊረዳው የሚችለው ነገር ነው ።

 2.     ሌላው እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ በደጃዘማች መሸሻ የልዑካን ቡድን ባስከፈተው የምስራቅ በር በኩል ያሉት የመነኮሳት መኖሪያ ቤቶች ሁኔታ  ነው። እነዚህ ቤቶች እጅግ በጣም ጠባብና ለአንድ ሰው መኖሪያ የማይበቁ  ብቻ  ሳይሆኑ ምንም ዓይነት ለኑሮ  መሰረታዊ  የሆነ ነገር ለምሳሌ መታጠቢያ  ቤት የሌላቸው ናቸው

 3.    በተለያዩ  ጊዜያት የገዳሙ ማህረሰብ መኖሪያ ቤቶቹ በተገቢው ሁኔት እንዲሰሩና  ቤተመቀዶሶቹም እንዲታደሱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምንም ዓይነት አዎንታዊ መልስ ሊያገኝ አልቻለም።

3.4    በቅድሚያ የሡልጣን ሱሌማን አዋጅ ኢትዮጵያውያን ቤተክርስቲያናቸውን እንዳደሱ ሲያስረዳ “በኢየሩሳሌም   የሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያዊው አባ ዮሐንስ ትጋት በ1500 ዓ ም መታደስ ጀመረ። የማደሻውም ገንዘብ ከኢትዮጵያ መንግስትና ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ዘንድ የተላከ ነው” ይላል።

 1.     በአንጻሩ በዴር ሡልጣን ላይ የይገባኛል  ክርክር ከተጀመረ በኋላ ባለቤቱ በትክክል እስኪረጋገጥ መንግስት ኃላፊነቱን ወስዶ ያሳድሰዋል በሚል ምክንያት ኢትዮጵያውያንን ከማደስ አግዷል።

 2.   ገዳሙ ለረጅም ዘመን ያለእድሳትና  ጥገና  መቆየቱ ለተመልካች ዘንድ ተከታታይ ማጣት ሊመስል ይችላል።ነገር ግን ለኢትዮጵያውያኑ ጥያቄ ተገቢ መልስ ከማጣት እንጂ በዚህ ውስጥ መኖሩ ተመራጭ ሆኖ አይደለም።

 3.     እንግዲህ በገዳሙ የሚኖሩ አባቶች መብት የተነፈጋቸው  መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። ምክንያቱም ሰውን ወደ በረዶነት በሚለውጥ ክረምትና  እጅግ በሚሞቅ የበጋ ሐሩር ለኑሮ በማያመች ቤት ውስጥ ሰውን አፍኖ ማኖር በሃያ  አንደኛው መቶ  ክፍለ ዘመን ያለ ማሕበረሰብ ፍትሃዊነት ወይም ሰብዓዊነት ይለዋል ብሎ  ማሰብ ያዳግታል። ቅጣት ነው ካልተባለ  በስተቀር ። ስለሆነም የሚመለከተው ሁሉ ትኩረት እንደሚስጥበት ተስፋ  እናደርጋለን።

 4.    በመጨረሻም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የጥቁር ሕዝብ ሁሉ መመኪያ  የሆነውን ይኸንን ታሪካዊ ቅርስ መጠበቅ  የገዳሙ ማህበረ መነኮሳት ሃላፊነት ብቻ አለመሆኑን ሊረዱት ይገባል። ገዳሙና  መነኮሳቱ የረጅም ጊዜ መከራን ጉስቁልና  አሳልፈዋል።

የዴር ሱልጣን ገዳም ለኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ክርስትና  ከቅኝ ግዛት በኋላ ወደ አፍሪካ የገባ ሳይሆን መሰረቱ እንደሆነና በኢየሩሳሌም ያለንን ድርሻ በአግባቡ መብት ተጠብቆ እንደሌሎች አገሮች ገዳሞች ሁሉ ተሟልቶ ለማንኛውም ጎብኚ ሲታይ አሁን የሚገኝበት አሳዛኝ ገጽ እንዲቀየርና ፡መነኮሳቱ ሰብዓዊ ክብር ተገፈው የሚኖሩበትንና፥ በተለይ በትንሣኤ በዓል በየዓመቱ ከኮፕቶች ጋር ያለው ግብግብ እንዲቆም፡ ሲሉ ዛሬ በገዳሙ ውስጥ ስለገዳማቸው ክብር በጉስቁልና  እየኖሩ፡ እየተደበደቡና እንደሌላ ፍጡር እየታዩ ፡ግን በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ እያለፉ ዳዊት እየደገሙ ለዚህ ትውልድ ባደረሱ አባቶችና  እናቶች ስም ሁሉም ተገቢውን ስራ እንዲያከናውንና ኃላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን ልንጠይቅ እንወዳለን። ይህ ጊዜ አዲስ ምዕራፍ የምንጀምርበት ነው። ስለሆነም ከምንግዜውም በላይ የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መነሳት አለብን። የገዳሙን ታሪክ በሚገባ አጥንቶ ለሌላው ማሳወቅም ይሁን ሕጋዊ ወይም ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ መፈለግ ለቀጣይ ትውልድ የምናስቀምጠው ስራ አይደለም። በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሁሉ የገዳሙ ታሪክ በማጥናትም ሆነ የሕግ፡ የገንዘብና  የሌላ  ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ጥሪያችንን እናቀርባለን።”  የጥቅሱ ጽሁፍ መጨረሻ

 

የዴር ሡልጣን መድሃኔዓለምና ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ገዳማትን ተባብረን በአንድነት ባለመቆማችን በአሳዛኝ ገጽታዎች ላይ የሚገኙ ቢሆኑም እነዚህ ገዳሞቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግፍ ተሰቅሎ ሞትን ድል ነስቶ እኛን ነጻ አውጥቶ ከተነሳበት የመቃብሩ ቦታ ከዋናው ጎልጎታ ጋር ተያይዞ የሚገኘ በመሆኑ ልዩ ግምት የሚሰጠው ታላቅ ክቡር  መንፈሳዊና ሀገራዊ ቅርስ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተን ልናስክብረው ይገባል ፡፡ ሌሎች የገዳም ድርሻ ይዞታቸውን እንደፈለጋቸው  በፈለጋቸው ጊዜ አስፈላጊውን እድሳት ማድረግ ሲችሉ ፡ እኛ ግን ዝርዝሩን ባለማወቃችን ባለን አቅም ተባብረን ለመቆም ባለመቻላችን የነበረንን ይዞታችንን ከማጣታችን በላይ በያዝነው ቦታችን ላይ ደግሞ ምንም ዓይነት እድሳት እንዳናደርግ አግደው ገዳማችን እንዲፈርስና ለቀን እንድንሄድ የሚደረግብን እጅግ ዘግናኝ ግፍ እንኩዋንስ ለኦርቶዶክሳውያን ቀርቶ ለማንም ኢትዮጵያዊ የሚቆጭ ስለሆነ ሁኔታውን ተገንዝበን አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንድንችል አሳዛኙን በእኛ እጅ ያለው የዴር ሱልጣን ገዳም ገጽታ በጥቂቱ ቀጥሎ ይመልከቱ ።

 

ንግስት እሌኒ በ320 ጎልጎታ  አሰርታ እስክ 18ኛው ክፍለ ዘመን በጃችን የነበሩንን መቅደሶች በግፍ ተነጥቀን በመጨረሻ የቀረንን በታላቅ ችግር ላይ የሚገኙት የዴር  ሡልጣን መድሃኔዓለምና የቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ገዳማት ፤ የውጭውና ፡ የውስጡ ገጽታችናና መነኮሳቱ የሚኖሩበት ትናንሽ አሳዛኝ መኖሪያ ቤቶች ይዘቶች፡

 

 

 

 

 

 

ቤተልሄም ደብረ ሰላም ኢየሱስ ገዳም በ1980 ዓ ም የተመሰረተ

የቀደሙ አባቶች በገዙት የግል ትንሽ ቤት ላይ የተመሰረተው የቤተልሄም ደብረ ሰላም ኢየሱስ ገዳም በፍልስጥኤም ግዛት ውስጥ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደበት በዋናው መቅደስ አጠገብ በቁልፍ ቦት ላይ ይገንኛል።

  ገዳሙ የሚገኘው በፍልስጥኤም ግዛት ውስጥ በመሆኑ የኢየሩሳሊም ታክሲ ወደ ቤተልሄም እንዲገባ የእስራኤል መንግስት ስለማይፈቀድ  ወደ ገዳሙ ከኢየሩሳሊም lተነስቶ ለመሄድ ያለው አማራጭ ፣  በጉዞ ድርጅቶች  የሚመጡ የቱሪስቶች አውቶቡስ ፣  በግል ኮንትራት መኪናዎችና  በተወሰነ የጉዞ ስዓት ጠብቆ ቤተልሄም  መሃል ከተማ ድረስ ብቻ ከኢየሩሳሌም የሚመጣው የከተማ አውቶቡስ ተሳፍሮ  ከአውቶቡስ ተራ  ታክሲ ይዞ ወይም በእግር በመጓዝ ነው ። ይህ ደግሞ ለአዲስ እንግዳ አስቸጋሪና አስፈሪም ስለሆነ በቀጥታ ከኢየሩሳሌም ገዳሙ ድረስ እንደልብ ለመመላለስ የሚያስችል የገዳሙ መኪናና  በገዳሙ ማህበር የተሰሩት ማረፊያ ቤቶች አስፈላጊ ነገሮች እንዲሟሉ የምዕመናንን ድጋፍ ይፈልጋል። ይህ ደግሞ ምዕመናን ገዳማቸው ዘንድ ቀርበው ችግሮችን በመረዳት የገዳሙን አገልግሎት ማጠናከሩ  ለምዕመናን ታላቅ መንፈሳዊ በረከትን ሲያስገኝ፣  የገዳሙ እድገት ደግሞ  ለቤተክርስቲያናችንም ዋስትና ይፈጥራል።  

 

 በአምላክ ፈቃድ በግላቸው የሚጎበኙ ምዕመናን እንዚህን መኖሪያ ቤቶች ተመልክተው ያሉትን ችግሮች በመቋቋም በቤተልሄም ማረፉ ታላቅ መንፈሳዊ እርካታን ስለሚሰጥ በግል የኮንትራት ትራንስፖርት በመያዝና ፡ በከተማው አውቶቡስ ተሳፍሮ  በአካባቢው ታክሲ በመጠቀም በገዳሙ ክፍሎች በማረፍ ፣ ከገዳሙ ደጋግ አባቶች በሚያገኘት ድጋፍ   ምግባቸውን እየሰሩ   በራስ አገዝ የጉዞ ጉብኝት ዘዴ በመጠቀም ለገዳሙ ምንም ገቢ ከማያመጡት ክፍሎች ገቢ እንዲያገኝና ከገዳሙ አባቶች ጋር ለመቀራረብና ስለገዳሙ ችግር የመረዳትና  አቅም በፈቀደ ለማገዝ ጥሩ አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡ 

 

ለገዳሙ አባቶች ለምኖ ማሰራት እጅግ ከባድና ብዙ ሂደትም የሚፈልግ ነው። ምዕመናኑ በዚያ በማረፍ ዓይናቸው ያየውንና በየጊዜው የጎደለውን ጥቂት ስራዎች መስራት መጀመር ወደ ትልቅ እንደሚያደርስ  በማመን  ፣ የገዳሙ አስተዳዳሪ መነኮሳት ድጋፍ ካገኙ ለመስራት ባላቸው በጎ ፈቃድ ለገዳሙ በጣም አንገብጋቢ ስራዎችን  ለማከናወን ተችሏል።

 ምዕመናን በአጠገባቸው ሆነው ባደረጉላቸው ድጋፍ ከደስታቸው ብዛት የጸሎት ስራቸው ሳይቋረጥ  ሌት ከቀን ሰርተው ፡ ቆፍረው እንደንብ በመብረር ያለዕረፍት በሚሰሩ አንድ የገዳም አስተዳዳሪ አባትና ለገዳሙ ፍቅር ባላቸው ምዕመናን ጥረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ በሚያስደንቅ ፍጥነት ከተከናወኑት ስራዎች ዋና ዋንዎቹ ስንመለከት፦

 • በቆሻሻ  ተሞልቶ ተቀብሮ የነበረውን ዋሻ  ቆፍሮ ተክፍቶ የካቶሊኮቹ Milk Grotto / የወተት ዋሻ በመባል የሚታወቀውን ዓይነት አምሮ ተሰርቶ  የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መቅደስ ከልጇ አጠገብ እንዲከፈት ተደርጓል።

 • ከመቅደሱ መግቢያ ላይ ተለግዶ የመቅደሱን መውጫና መግቢያ አጣቦና መንቀሳቀሻ ያሳጣውን ቤት ባለቤት ነን ለሚሉት 19 ሺህ ዶላር ግምት እዚያው ባረፉ ቤተሰብ  ተከፍሎ ቤቱ ፈርሶ የገዳሙ ግቢ ሰፍቶ እንደልብ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል አዳራሽ ሲሰራ  አንዳንድ የሚጎድሉትም ነገሮች ወደፊት ይሟላሉ። 

 • ክላይ ያለው ዋናው መቅደስ መቆሚያ በረንዳ የሌለውና በአጠገቡ ለረዥም ጊዜ ተዘገተው ከነበሩ ክፍሎች ጋር በመቀላቀል እንዲሰፋና ሌሎቹም ክፍሎችን አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ታድሰዋል 

 • ከመቅደሱ ወደ ሌሎቹ ክፍሎች ለመሄድ የሚያስችል ጣራና በረንዳ በመጨመሩ ምዕመናን ቦታ ሲጠብ የሚያስቀድሱበት ተጨማሪ ቦታን ፈጥሯል

 • በዋናው መቅደስ ፊት ለፊት ተዘግተው የነበሩ ቤቶችም ለተጨማሪ የእንግዳ ማረፊያ እንዲሆኑ ታድሰዋል

 • በውስጡ የነበረውን ጠበል ጥሩ የሆነ  የጠበል ቤት ተሰርቶ ምዕመናን በጥሩ ሁኔታ የጠበል አገልግሎት በማግኘት ላይ ናቸው።

 • ከገዳሙ ጀርባ የነበረ ቦታ ምዕመናን በሚደረገው እንቅስቃሴ በመደሰት በአጭር ጊዜ ገንዘብ ሰብስበው እንዲገዛ ተደርጓል

 • ካንድ ሰው በላይ የማያስቆመው የምግብ መስሪያ ክፍል በተሻለ ተስፋፍቶ ተሰርቷል። ሌሎች መሰራት ያለባቸው ስራዎች እንዲሁ ይቀጥላሉ።

 እነዚህ ክንውኖች በአጭር ጊዜ የተሰሩ በመሆናቸው ቀሪው የትራንስፖርቱና ለተሰሩት ማረፊያዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በሟሟላት በቅርብ ለምዕመናን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንዲቻል ይህን የመሰለው ተቀራርቦ በአንድነት የመስራቱ ሂደት ታላቅ ተስፋ ሰጭ ሆኗል፡፡

 

ይህም አሰራር በምዕመናን በይበልጥ ሲታወቅ ሁሉም እንደሚድሰትና  የተቀሩትን ገዳሞችና ያሉን ህንጻዎቻችንን አጠናክረን እኛም በራሳችን ገዳሞች ኦእንደሌሎች ሁሉ በራስ አገዝ ለሚሳለሙ ምዕመናን የትራንስፖርትና የሆስቴል አገልግሎትን በየገዳሞቻችን እንዲኖር በማድረግ ምእመናን የበለጠ ገዳማቸውን አውቀው እንዲረዱ በጸሎታቸው እንዲረኩና ከብዙ ከዓለም ክፍል የሚመጡ ምዕመናን  ማስጎብኘትና ማሳወቅ ፣የኢየሩሳሌምን ገዳማት ከማጠናከር አልፎ  በኢትዮጵያ የተዳከሙ ቤተክርስቲያናትንና  ገዳሞቻችንን እንድናጠናክር እንደሚጠቅም በማመን ክንውኑ ለሁሉም  ተጋርቷል፡፤  

የቤተልሄም ደብረ ሰላም ኢየሱስ ገዳምን ከነስራ እንቅስቃሴውን ክንውኖች ከታች በተመለከቱስ ፎቶግራፎች ይመልከቱ 

image26.jpg
image27.png
image4.jpg
image6.png

 

ቅዱስ ፊሊጶስ ገዳም በ 1883  ዓ ም /ኢየሩሳሌም ኦሮጌው ከተማ ጎልጎታ /

 

ይህ  ገዳም  በኢየሩሳሌም አሮጌው ከተማ ውስጥ (ጊታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀሉን ይዞ በተጓዘበት በ8ኛው ምዕራፍ ቪያደሎሮሳ መንገድ)  በቅድስት ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአስተዳደሩ ጽህፈት ቤትና   የቅዱስ ጳጳሱ መኖሪያ ቤት ግቢ  ውስጥ የሚገኝ ሲሆን  በሃዋርያት ስራ ምዕራፍ  8 ፡ 26 – 39 እንደተጠቀሰው በ34 ዓመተ ምህረት በመንፈስ ቅዱስ  በገለጽለት መሰረት ኢትዮጵያዊውን  ጃንደርባው  አጥምቆ ክርስትናን በጠዋቱ  ወደ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ እንዲስበከ ላደረገው የቅዱስ ፊልጶስ መታሰቢያ  ገዳም ነው፡፡ ገዳሙ በጣም ጠባብ በሆነ ክፍልና ግቢ ውስጥ በመሆኑ፣  በስም ቢኖርም አገልግሎት  አይሰጥም።  ይህ ለኢትዮጵያ ቀደምት ክርስትናን የመቀበል ታሪክ በሃዋርያት ስራ ተመስክሮ ይገኛል። 

 

  ኢትዮጵያዊውን ጃንደርባ  ያጠመቀው የ ቅዱስ  ፊሊጶስ  መታስቢያ  ገዳምን ካለበት ስርቻ አውጥቶ  በግልጽ በሚታይ ቦታ ላይ መደረጉ ለቤተክርስቲያናችን ጥንታዊነትና ለሃገራችን ኢትዮጵያ  ታላቅ ሃውልት ይሆናል።  በቶሎ ለመተግበርና Lገዳሙ ካለው ታሪካዊነት አኳያ  በገዳሙና በምዕመናን እርዳታ የቁልፍ ተከፍሎ የታደሰው  በ8ኛው ምዕራፍ ፊት ለፊት የሚኘው  ህንጻ ውስጥ እንዲገባ ቢደረግ ፣ ከተለያየ ዓለም የሚመጣው ጎብኝ  8ኛውን  ምዕራፍ ለመጎብኘት ሲመጣ  በፊት ለፊት በቅድስት አገር  ኢየሩሳሌም   እትዮጵያዊውን ጃንደርባ  ያጠመቀው  የቅዱስ ፊሊጶስ መታ)ስቢያ ገዳም  (የሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 8 ቁጥር 26 ፣39) ተብሎ  ከሰንደቅ ዓላማችን ጋር  በተለሲያዩ  ቋንቋ ተጽፎ እየተመሊከት ዳሙን  ገብተው  እየተሳለሙ  የኢትዮጵያን  ቀደምት የክርስትና አገር መሆኗን ከማንም ሃውልት በላይ ይረዳሉ።  በተጨማሪም   ከሰባተኛው ምዕራፍ  ጀምሮ እስከ መንበረ ጵጵስና ያሉትን  በቁ-ልፍ ተይዘው ያጣናቸውን ሱቆችና ቤቶች  ምዕመናንን በማስተባበር  በመግዛት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ በጎልጎታ  ያላትን  ይዞታ  ከምማጠናከሩም በላይ የተለያዩ  ኦርቶዶክሳዊና ኢትዮጵያዊ  ቅርሶች ማሳያና መሸጫ በማድረግ  ለገዳማቱ ታላቅ ድርሻን ስለሚያበረክት  የገዳሙ  ማህበር በጀመረው የገዳማቱ  የማሻቻል ስራዎች  ይህንንም ወስኖ ከጀመረ  ሁሉም ምዕመናኖች በደስታ  የድርሻቸውን  ያበረክታሉ።    

 

 

በ1883 የተመሰረተው የቅዱስ ፊሊጶስ ገዳም ፣ የመንበረ ጵጵስና ጽሕፈት ቤትና የሊቀ ጳጳሱ መኖሪያ ቢት

በ1883 የተመሰረተው የቅዱስ ፊሊጶስ ገዳም ፣ የመንበረ ጵጵስና ጽሕፈት ቤትና የሊቀ ጳጳሱ መኖሪያ ቢት

 

በኢየሩሳሊም ቤተልሄምና ኢያሪኮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሌሎች ህንጻዎች

 

በቅድስት አገር ኢይሩሳሌምና አካባቢው ካሉን ገዳማቶች በተጨማሪ የገዳሙ አባቶች ግንኙነት በተቋረጠበት ወቅት አባቶች ተቸግረው በሞትና ስደት ምክንያትት ይዞታችን እንዳናጣ አርቀው አሳቢ የነበሩት አባቶቻችን ህንጻዎች ተሰርተው እየተከራዩ ለገዳሙ መነኮሳት መተዳደሪያ እንዲሆኑ አሰርተው ያስረከቡን የሚከራዩ ህንጻዎች አሉን።

 • በኢየሩሳሌም ከተማ ግርማዊት ንግስት ዘውዲቱ ያሰሩት ዘውዲቱ ህንጻ ተብሎ የሚጠራው ህንጻ/ኢየሩሳሌም

 • በእቴጌ ጣይቱ የተሰራ ህንጻ /ኢየሩሳሌም

 • ገዳሙ በቅርብ ያሳደሰውና ሌሎች ነባር ህንጻዎች ደብረገነት ኪዳነ ምህረት አካባቢ የሚገኙ ህንጻዎች

 • ኢያሪኮ ገብርኤል አጠገብ የሚገኝ

 • ቤተልሄም ኢየሱስ ገዳም አጠገብ

 • አሮጌው ከተማ ውስጥ በስምንተኛው ምዕራፍ ላይ/Old City 8 Station/በቁልፍ ማያዥ ተውስዶ የነበረ በቅርቡ ገዳሙ ማስለቀቂያ ክፍሎ ተረክቦ ያሳደሰው

የሊሎቹ ህንጻዎች ፎቶግራፍ ወደፊት የሚቀርብ ሲሆን ለጊዜው ግን ውብ ሆኖ በንገስት ዘውዲት የተሰራውና ዘውዲቱ ህንጻ እየተባለ የሚጠራው ህንጻ ከታች የተመለከተው ነው

የአጼ ምኒልክ ልጅ የሆኑት ያባታቸውን ፈለግ በመከትል ንግስት ዘውዲቱ ያሰሩት ዘውዲቱ ህንጻ

image7_edited.jpg

ምዕመናን እንዴት እንርዳ? የኛ ድርሻ ምን ይሁን?

ከላይ የተመለከተውን ጽሁፍና በፎቶ የቀርቡት ይዞታዎች ያለውን ከፍተኛ ችግር ያመለክታሉ፡፡ እየደረሰ ያለው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን በቅድስት ሃገር ለመሳለም እድል ገጥሞት የትንሣኤን በዓል ለማክበር የሄደ ሁሉ በየዓመቱ በትንሳኤ ምሽት የአንድ ዓይነት ጥንታዊ ኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ከሆንነው ግብጻውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችን ጋር ያለው ረብሻ፤ እጅግ አሳዛኝና አንድ መጽሃፍ ቅዱስ አንብበን በአንድ ጌታ የምንታመን መሆናችንን ላሰበ ልብን የሚሰብር ነው ።

 

የኢትዮጵያ ገዳማት የሚገኙበትን ይዞታ፡ የመነኮሳቱን አኗኗር ከሌሎቹ የካቶሊኮቹን ፣ የግሪክ፣ የራሽያ የሆኑ ገዳማት መቅደሶች፡ የንዋየ ቅዱሳት መሸጫዎቻቸውን፣ የእንግዳ ማረፊያዎችን፣ ለተሳላሚዎች ማረፊያና የጉብኝት ዝግጅት ፣ የትምህርት፡የመሳሰሉትን ለተመለከተ ከድህነታችን የመነጨ ብቻ ሳይሆን ስለሁኔታው በቂ ግንዛቤ ባለማኘታችንና በበቂ ባለመሳተፋችን ምክንያት ሁኔታዎቹ እጅግ ልብ በሚሰብር ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

 

 በመላው ዓለም ያሉ የኦርቶዶክስ ምእመናን ይህንን እውቀን ከጥንት አባቶች ያቆዩንን እንዳይጠፋብን እንድንሳተፍና ተገቢውን እንክብካቤ እንድናደርግ ፤ ዕድል ገጥሟቸው በየጊዜው ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ለመሳለም የሚመጡ ምእመናን ደግሞ እመሰራረት ታሪኩን ፡ ዛሬ ያለበትን ሁኔታና ችግሩን በጥልቅ በማየት ተሳትፏቸውን በማሳደግ ባላቸው አቅም፡ ዕውቀትና ገንዘብ በመሳተፍ ይዞታችንን እንድንገነባ የተዘጋጀ አጭር መነሻ ነው። 

 

ይህም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ጽህፈት ቤት ላቀረበው ጥሪ ምላሽ ጅማሮ ሲሆን ይህን ጉዳይ በጥልቅ የሚያውቁ  ብዙ ዕውቀት ያላቸው የሃይማኖት አባቶች፡ ሰባኪያን መምህራን፣ የተለያይ ሙያ ያላቸው ምዕመናን ፣ሁሉ ከተሳተፉበት መብታችንን ለማስከበር እንችላለን። ለምንጀምረው ጉዞ እንዲያስችለን ጠቃሚ ማስረጃ ሰነዶች፤ ቪድዮ፡  የታሪክ ማስረጃዎችንና የስራ ሃሳቦችና ፐሮጀክቶችን በመንደፍ ገዳሙን ለማገዝ  እንድንነሳ ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅሩን፡ ዕውቀቱንና ኃይሉን እንዲያጎናጽፈን በመለመን በትህትና አዳብሩት እንበርታ እንላለን።

ለመነሻ ውይይትና ተግባር ይጠቅማሉ ብለን ውይይት እንዲደረግባቸውና ብሎም ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ በመነኩሴ የቀረቡ፣ጥቂቶቹ ቀጥሎ ቀርበዋል።

 

 

የዴር ሡልጣን ገዳምን ለማስከበር

 

 1. በግፍ የተነጠቅነውን መብታችን ለማስመለስ የሚረዱ መረጃና ድጋፍ ዶኪመንቶችን ማሰባሰብ፡

 2. ምን ያህል የገንዘብ፡የህግ፡ የአዋቂ ባለሙያ ተሳትፎ፡ የዲፕሎማሲና ግንኝነቶች እንደሚፈልግ ማጥናት፡

 3. አስፈላጊ የሆነውን ገንዘብና መሰል ዝግጅቶችን ማደራጀት፡

 4. ልዩ ብቃት ያላቸው ኢንተርናሽናል የህግ ባለሙያዎችን ማፈላለግና መቅጠር፡

 5. ለእስራኤል ፓርላማ ጉዳያችንን የሚያስረዱ ብቃት ያላቸው ታዋቂ ሎቢስቶች(ተጸዕኖ ፈጣሪ) መቅጠር

 6. የዓለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በመገናኘት የሚደርሰውን ግፍ ማሳወቅ

 7. የዓለም ዓብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያን ጥንታዊነት ስለሚያውቁ ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ እንዲተባበሩ

 8. የህግ ሙያ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ማድረግ። 

 9. በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት አስተዳደር ቅድስት አገርን ለመሳለም የሚመጡ አሳውቆ በአባልነት ማሳተፍ

 10. በሃገር ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም ያለንን ቅርስ በማሳወቅ ሁሉም በአቅሙ እንዲሳተፍ በማድረግ ሁለገብ እንቅስቃሴ ከተደረግ የዴር ሱልጣን አከራካሪ የሆነውና ልንነጠቅ ያለው ደባ ዕልባት ሊያገኝ ይችላል። 

ከላይ የተዘረዘሩት ስራዎች ከፍተኛ መደራጀትንና የገንዘብ ዓቅም ስለሚጠይቅ እንኩዋንስ መጨረስ ለመጀመርም

ከባድ ይሆናል። ነገር ግን ሃምሳ ሎሚ ላንድ ሰው ሸክም ነው ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ እንደሆነ ሁሉ በዴር ሱልጣን 

ገዳማችን ያለአግባብ በኣባቶች ላይ የሚደርሰውን ግፍ በህግና  ክርስቲያናዊ በሆነ የሰላም መንገድ እጅግ አከራካሪ 

የሆነውና  ልንነጠቅ የሚደረገብንን ደባ ለማስቆም የሁሉንም ህብረት ይጠይቃል። ለመብቱ ጉዳይ ሁላችንም 

በምንችለው ተሳትፈን ማስከበር ከቻልን የእድሳቱን ስራ  መስራት ቀላል ይሆናል።

 በመነኩሴ ሃሳቡ ለውይይት ቀርቧል፡፡ የዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳማት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀበለበት፡ ተቀብሮ ከተነሳባት ዋናው ጎልጎታ ጋር ተያይዞ ያለ ታላቅ ክቡር የሆነ የገዳም ይዞታችን በመሆኑ ይህን  አሳዛኝ ገጽታ ለማሻሻል ቆርጠን መነሳት አለብን

 

 ቅዱስ ገብርኤል ኢያሪኮ ገዳም በ1920 ዓ  ም/ ኢያሪኮ ከተማ/ ገዳም ቆሮንቶስ አጠገብ 

የኢያሪኮ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ውብ ሲሆን በአጠገቡ የዘኪዎስ ሾላ ዛፍ፡ የነቢዩ ኤልሳ ጸበል ፡ ክፍ ብሎ ጊታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት የጾመበት የቆሮንቶስ ገዳምና ጥቂት ተጉዞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ልጅነትን እንድናገኝ ጥምቀትን የሰራበት የዮርዳኖስ ወንዝን አካቦ ያለ ገዳም ነው፡፡ ገዳሙ በተጨማሪ ዮርዳኖስ የነበረው የቅድስት ሥላሴ ታቦት በ1967  የአረብ እስራኤል ጦርነት  ገዳሙ በመመታቱና አካባቢው በፈንጂ በመታጠሩ ታቦቱን የነቡሩት አባት አሽሽተው በዚሁ ኢያሪኮ ገዳም በደባልነት ላለፉት 55 ዓመታት ተቀምጧል ። ገዳሙ ደጋግ ምዕመናን የለገሱት የሚከራይ ቤትም በአጠገቡ ያለ ሲሆን መንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዲጠናከር የሁሉንም ድጋፍ ይፈልጋል፡፡

kidanemeheret.jpg

ቅድስት ሥላሴ ገዳም በ1915 ዓም /ዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በግርማዊት እቴጊ መነን የተሰራ

 

ምንጊዜም መልካም ስራ በታሪክ ተቀምጦ ምስክር እንደሚሆን የቅድስት ሥላሴ ዮርዳኖስ ገዳምን በሚመለከት በተደረገው መረጃ ፍለጋ አስገራሚ የሆኑ ፎቶግራፎችና ስራውን በሚመለከት የፍልስጥኤም ኢንስቲትዩት ጥናት ማዕከል ላይ ሚስተር ገብርኤል ፖሊ/  Gabriel Polley :The Monastery, the Ethiopian Empress, and a Tale of Two Architects/ በሚል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያቀርበውን ጽሁፍ ታሪካዊ ሆኖ ስላገኘነው እንዳለ የእንግሊዝኛው ጽሁፍ ቀርቧል ፡፡

image19.png
image17.png
image22.png
image23.png

ያ እንደዚያ በሚያምር መልክ ግርማዊት እቴጌ መነን አስፋው አስርተውት የነበረው ውብ ህንጻ በ1967 የእስራኤልና አረቦች ጦርንት ክተመታ በኋላ በአሁኑም ጊዜ ያለው ገጽታው  ውብ የነበረውን ገዳም ዕይታ ያመለክታል ፡፡ ምንጌዜም አስከፊ በሆነው ጦርነት በ1967 የእስራኤልና ዓረቦች ጦርነት በመድፍ በመመታቱና ዙሪያው በፈንጂ በመታጠሩ ላለፉት 53 ዓመታት ተዘግቶ የቆየው የዮርዳኖስ ቅድስት ሥላሴ ገዳም አሁን ፈንጂው ተለቅሞ ስለጸዳ እንደገና  እንዲከፈት በመፈቀዱ የገዳሙ አስተዳደር  እንደገና ለመስራት የሚቻልበትን ሁኒታ ጥናት በማድረግ እንደገና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችልበትን ጉዳይ እየተከታተለ ነው። ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑና ለረጅም