የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፡ 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመላው ዓለም በርካታ ቤተ ክርስቲያናት ፣ ገዳማትና ምዕመናን አሏት ። አምልኮተ እግዚአብሄር ፡ በሳል የአስተዳደራዊ ፍትሃዊነት፡ ለዕምነት ጽናት ፡ በረሃና ውቅያኖስ አቆርጦ ለእምነት መሞት ፣ ከራስ ጥቅም ይልቅ ሃብትና ንብረትን ለእግዚአብሄር የማዋል ምግባር ጥንት በአባቶቻችን አኩሪ መሰረት የነበረን መሆኑ በቅዱሳት መጽሃፍትም ተጠቅሰዋል፡፡

በዘመነ ብሉይ

·       ደገኛው የምድያም ካህን ራጉኤል/ዮቶር ያለምንም ጥቅም  ፍለጋ ታላቁን ነቢይ ሙሴን አስጠግቶ ፥ህይወቱን አትርፎ፣ ልጁን ኢትዮጵያዊቷን ሲፓራን ድሮለት ልጅ እንደወለደችለት  በኦሪት ዘጸዓት፡ ም 2 ፡ 15-22ና ኦሪት ዘኁልቁ ም 12፡1 

·       ዮቶር የሙሴ አማት የጠለቀ ያስተዳደር ችሎታ እንደነበረው ፥ ሙሴ ብቻውን ሲደክም ሰዎች መርጦ ፥ኃላፊ እሰልጥኖ ፥ሃላፊነትን እንዲያካፍል መምከሩ ፡ኦሪት ዘጸአት ም፡ 18፡ 18-24 

·       ኢትዮጵያዊው የንጉስ ባለሟል አቤሜሌክ ስልጣኑን ህይወቱን ሊያሳጣው የሚችል ቢሆንም ለዕውነት በመቆም  ቆራጥ አቋም ወስዶ ፥የነቢዩ ኤርምያስን ህይወት ከሞት ማዳኑን  በትንቢተ ኤርምያስ ም 38 ፡7-13   

·        ንግስተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰለሞን  የሰጠውን ጥበብና ዕውቀት በአካል ተገኝታ ለማየት በዚያን ዘመን ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ስትሄድ "ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቁ ሰጠችው ፣ የሳባ ንግሥት እንደ ሰጠችው ያህል የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር " ተብሎ ተመዝግቧል ። መጽሃፍ ነገስት ቀዳማዊ ፣  ም 10፡ ቁ 1-13

     በዘመነ ሀዲስ፡

·       በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ቂ 26-39 ኢትዮጵያዊው ጃንደርባ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ የነቢዩ ኢሳይያስን ትንቢት እያነበበ ሲመለስ በመንፈስ ቅዱስ በተላከው ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ተጠምቆ ክርስትናን በ34 ዓመተ ምህረት ኢትዮጵያ አስገብቷል። 

·       በኢትዮጵያ ነገስታት ከቤተ መንግስት እስከታች ባለው ሕዝብ በይፋ ክርስትና ከ330 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሰላም የተሰበከባትና ጥንታዊ ከሚባሉት አንዷ ስትሆን ከሮምና ሶርያ በአረመኔ ነገሥታት ከሚደርስባቸው ጥቃት ሸሽተው የመጡ አባቶችንም ተቀብላ በሰላም ኖረው ፣ አስተምረው በስማቸው ቤተክርስቲያን ተሰይሞ አሁንም ይዘከራሉ ።

·       እንደ ቅዱስ ያሬድ ያሉ ምጡቅ የዜማ ፣ የሥነ ጥበብ አዋቂዎች ፣ በራስዋ በግእዝ ቋንቋ  የተጻፉ የዜማ ፣ ቅኔ ፣ የስነ ፈለግ ፣ ህንጻ ፣ መድሃኒት ፣ የተለያዩ የጸሎት መጻህፍትና ዓለም ለትክክለኛ መረጃ ቅርስነት የመዘገበው በግእዝ የተጻፈ ኢትዮፒክስ ተብሎ የሚጠቀስ መጽሃፍ ቅድስ አሏት ።  

·       በህገ ልቡና ከካም ፣ ኦሪትን ከንጉስ ሰሎሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ መምጣት ጀምሮ ለሺህ ዓመታት ፣ አዲስ ኪዳንን ክ34 ዓመተ ምህረት ጀምሮ አምላክ የተመስገነባት ፣ ቅድስት ሃገር ኢትይዮጵያ በአክሱም የሙሴ ጽላት፡ በግሼን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰበት ግማደ መስቀል ይገኛል።

·       ዓለምን የሚያስገርመው የቅዱስ ላሊበላ ቤተክርስቲያናት፡ የጣናና ሌሎች በርካታ ድንቅ ቤተክርስቲያናትና ገዳማት በብ።ዛት አሉ

·   ከቤተክርስቲያናትና ገዳማት ጋር የተጣመሩት የአብነት የትምህርት ቤቶችዋም በግእዝና በቅኔ የበለጸጉ ካህናት ፣ ዲያቆናትና መምህራን ያወጣሉ።

· የእስልምና እምነት ሲጀመር ነቢዩ መሃመድ የፍትህና የነፃነት ሃገር ወደሆነችው ኢትዮጵያ በስደት የላኳቸው ተከታዮቻቸው በሰላም ኖረው ለእስልምና እምነት መሰረት ሆና የአብሮነት ባህል ዳብሮባታል።

የቤተክርስቲያንዋ ፈተናዎችና ጽናት 

·      በተለያየ ዘመናት በተነሱት በዮዲት ጉዲት ፣ የክርስትናውን ዓለም ባንቀጠቀጠው በኦቶማን ቱርክ አጋዥነት በተነሳው በሃገር በቀሉ ግራኝ መሐመድ ፣ በፋሽስት ኢጣልያ  ወረራዎችና በ1960ዎቹ በሃገራችን የተጀመረው የማርክሳዊ አስተሳሰብ መንግስትን ማናጋት ብቻ ሳይሆን  በሃይማኖት ጠልነቱ ፣ በአስተዳደርዋ ጣልቃ የመግባት ፣ ንብረትዋ ዘርፎ ፣የዘር ና የሃይማኖት አክራሪነት በማስረጹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጥቃት ኢላማ ተደርጋ ፣ ቤተክርስቲያናት ገዳማት ፣ ንዋየ ቅድሳትና መጻህፍት በእሳት እንዲጋዩና እንዲዘጉ ፣ ካህናቶች ፣ ዲያቆናትና ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲታረዱ ቢደረግም ፣  በእግዚአብሄር ድጋፍ ፣ በየጊዜው በሚያስነሳቸው አቡነ ተክለሃይማኖትን የመሳሰሉ ታላላቅ የወንጌል አምዶች አባቶች ፣ እስከዛሬ ዓለምን የሚያስገርሙትን  ቤተክርስቲያናትን የቀረጹትን ቅዱስ ላሊበላን በመሰሉ ነገሥታት ፣ ትውልድ ተሻጋሪ እውቀትና የቤተክርስቲያን ወርቃማ ዘመን ያሰኙ እነአፄ ዘርዓ ያዕቆብን መሰል መሪዎችና በጠንካራ የአማኞችዋ ጽናት እስካክሁንም ወደፊትም ትቀጥላለች 

· ጥንታዊ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት ዛሬ ያሉበትን ሁኔታ በጥቂቱ ስንመለከት፣

                   ·  እነቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጳውሎስ ያስተማሩባቸው በዮሐንስ ራዕይ በምዕራፍ 2 ና 3 የተጠቀሱት 7ቱ የመጀመሪያው ምዕተ ዓመት                                ቤተክርስቲያናት ከተሞች (ኤፌሶን ፣ ስምርኔስ ፣ ጴርጋሞን ፣ ትያጥሮን ፣ ሰርዴስ ፣ ፊላደልፊያና ሎድቅያ) የክርስቲያኖች ቁጥር ከግማሽ                           ሚሊዮን በታች እጅግ አንሶ በዛሬዪቱ ቱርክ ቦታና መብትም የላቸውም ።  

    ታላቁ ቁስጠንጢኖስ ከጣኦት አምልኮ ነጻ የሆነሽ አዲስ ንጹህ ከትማ ብሎ የቆረቆራት የኮንስታንቲኖፕል ከተማ ዛሬ ስሟ ኢስታንቡል  ተብላ የክርስትና ዝናዋ ሲወድም ሃጌ ሶፍያ ብሎ በወርቅ ያሰራት ቤተክርስቲያን በኦቶማን ቱርክ በ1453 ዓመት ምህረት በገጠማት ሽንፈት ወርቋ ተዘርፎ ወደመስጊድነት ተቀይራ ስትኖር ቆይታ በ1935 ዓመት ምህረት ወደ ሙዚየምነት ተቀይራ በሁሉም ክርስቲያን ስትጎበኝ የነበረችው በ2020 ዓመተ ምህረት በድጋሚ ወደመስጊድነት ተቀይራ በሙዚየምነት እንኳን በክርስቲያኖች መጎብኘትዋ ቀርቷል።

  •        የቅዱስ ጳውሎስ የስብከት መጀመሪያው ደማስቆ የሚገኝባት ሶርያ ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያናቶችና ቅርስ የነበረባት ሶርያ ባለፉት 11 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ስትወድም ዓለም እያያቸው አላዳናቸውም። ተመናምነው የነበሩት የተዋህዶ ኦርቶዶክሳውያንም       ሲመናመኑ፣ በአጠቃ፤ኡ የሃገሪቱ ሕዝብ ላይም አሳዛኝ ጉዳት ደርሷል ። ከጦርነት በፊት በሶርያ ክነበረው ሕዝብ አብዛኛው በነበረበት ቤት አይኖርምም። በግልጽ ክርስቲያኖች ሲታረዱ ፣ ሲፈናቀሉ ፣ ከተማቸው እንዳል በእሳት ጋይቶ ሲወድም ፣ የመላው ዓለምም እያየም አያይም ። እየሰማም አይሰማም ። እንደሩዋንዳ ወደፊት የፌዝ ይቀርታ የል ይሆናል።አንድ የነበረችው ቤተክርስቲያን 

                                  አንድ የነበረችው ቤተክርስቲያን 

  • አንድ የነበረቸው ቤተክርስቲያን በ451 ዓመተ ምሀረት በአራተኛው የኬልቄዶን ጉባኤ ስትከፈል የጥንቱን የኦርቶዶክስ ተዋህድ እምነት         አንቀይርም ያሉት /ኦሪዬንታል ኦርቶዶክስ/ በመባል የሚታወቁት 6ቱ እህትማማች አብያተ ክርስቲያናት (ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ ፣ አርመን       ሶርያ ፣ ሕንድና ኤርትራ) ዛሬ በጠቅላላው 80 ሚሊዮን ሲገመቱ ፣ ከዚህም ከፍተኛው 47 ሚሊዮን  በኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን በግብ         23 ሚሊዮን በቀሩት ሃገሮችና አማኞቻቸው ተሰደው ባሉበት የዓለም ሃገሮች ይገኛሉ።

ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንም እየገጠማት ያለውን የህልውና ትቃት ፣ የምዕመናኑ በኤኮኖሚ መዳከም ከላይ ያየናቸው የሌሎቹ 

እጣ እንዳይገጥማት ፣ ሌላ ከውጭ የሚረዳት ስለሌለ በሃገርና በመላው ዓለም የምንገኘው ኦርቶዶክሳውያን ከህልውና ጥቃት እንድትጠበቅ ፣

ያሉት አማኞችዋም ተጠናክረው ሌሎችም እየተጨመሩ እንዲከተሏት ፣ የኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ አገልግሎት/ORTHODOX TEWAHEDO 

MISSIONARY SERVICE /ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ቁ 13-16 እናንተ ጨውና ብርሃን ናችሁ 

ብርሃናችሁ ለሌሎችም ይብራ ብሎ ባስተማረን መሰረት እርሱ ወደ አዘጋጀልን ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ለመውረስ ከአጥቢያችን ቤተክርስቲያን 

በተጨማሪ በምንችለው ሁሉ እንድንንቀሳቀስ የመነኩሴ ድህረ ገጽን በማዘጋጀት በኢትዮጵያ ፣ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌምና በተቀረው ዓለም 

ስላሉን ቤተክርስቲያናትና ገዳማት አውቀን እንድንረዳ ፋና በኢትዮጋት/FanaBEthioGat/ በሚል የስራ ርዕይ የመነሻ የተግባር መርሃ ግብር ዝር

ዝሮች አይታችሁ ሃሳባችሁንና ተሳትፋችሁን አጋሩን አብረን ለቤተክርስቲያናችን እንስራ።

በውጭ ዓለም

ጥንት ኢትዮጵያውያን ለትምህርት ሲላኩ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ቢለመኑ እንኩዋን  በውጭ ሳይቀሩ ወደሃገራቸው እምቢ ብለው ይመለሱ የነበረበው ሂደት፣ በሃገር ተከብሮ በሰላም የመስራትና ፡ የመኖር ዋስትናና ፡ የሃገር ፍቅር ፡ ተንዶ  ችግርና ረሃብ በመንገሱ፣ ላለፉት 45 ዓመታት ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም ተሰደዋል። ኢትዮጵያዊ ባለበት ቦታ ሁሉ ቤተክርስቲያን፣ የሃገር ልብስ፣ እንጀራና ወጥ የሚገኝበት ያበሻ ምግብ ቤት አብረው ተሰደዋል ። ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሆነ ሁሉ ለሁለት ሺሀ ዓመታት በመላው ዓለም የተበተኑ እስረኤላውያን በሄዱበት ሁሉ በንግድ ፡በትምህርት በመጎልበት ፣ ዕውቀትና ንብረት በማፍራት ከምድረ ገጽ ጠፍታ የነበረችውን እስራኤል እንደገና እንደወለዷት ሁሉ፣ የኢትዮጵያውያንም በመላው ዓለም መበተንና ማደግ ከስታ የጠቋቆረችውን ኢትዮጵያ እንድታብብና መልካም ፍሬ እንድታፈራና ለቤተክርስቲያናችንም ድጋፍ በመሆን ዕጣዋ ያማረ እንደሚሆን መገመት ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። እግዚአብሄር ከኛ የበለጠ የሚያውቅና የወደደውን እንደሚያደርግ ሁሉ ሁኔታዎችን ስንመለከት፦ 

·       ዛሬ  በአብዛኛው የምዕራቡ ዓለም ቤተ ክርስቲያናት  እየተዘጉ፡ አማኝና አምልኮተ እግዚአብሄር የሚፈጽም  በመጥፋቱ፡ ወደ ንግድ ቤት እየተለወጡ  ባለበት ዘመን ብዙዎቹ ቤተክርስቲያናት በኢትዮ ጵያ ኦርቶዶክስ ዓማኞች  እየተገዙ ፡አዲሶችም  እየተገነቡ ናቸው።

·       በልዩ ስርዓት የሚቀርበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ  ጸሎት በመላው ዓለም እየፈሰሰ  ፣ ታቦተ ሕግ በፖሊስ ሞተር እየታጀበ በታላላቅ የአሜሪካ፡ አውሮፓና  ካናዳ  ከተሞች ጥምቀት  እየተከበረ ፣ ይገኛል።

·       ዓለም ትክክለኛው አምላክ ለሙሴና አሮን ባዘዘው ክብር የተላበሰ እምልኮትን በማየታቸው ብዙዎች ይህ ነው አምልኮተ እግዚአብሄር እያሉ እየተጠመቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታይ እየሆኑ ናቸው።

·       ሃብትና ገንዘብ ይዞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ቤተክርስቲያን እናስፋፋ ተብሎ መንግስት ወይም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ቢጠይቅ አንድም ቤተ ክርስቲያን ተፈቅዶ ለመስራት አይቻልም ነበር ። አሁን ግን በንቂያው የኦርቶዶክስ የአምልኮት ስርዓት መሰረት የተመሰረተችውና ልዩ የራስዋ የቅዳሴ ስርዓተ አገልግሎት ለመላው ዓለም እንዲታወቅ እምላክ የፈቀደው ነው ለማለት በሚያስችል ግንዛቤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ቅዳሴ በሃያልዋ አሜሪካ ባሉ በመላው 50 ስቴቶች ከተሞችና፡ መላው ዓለም  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተክርስትያን  ግንባታ እያበበ ነው። 

 ይህ ቀላል ይመስላል ግን እጅግ ልዩ አጋጣሚ ሲሆን ቤተ ክርስትያናችን በመላው ዓለም መከፈት ሲያስደስት ሲጀመሩ ከዕምነት ፍቅር አንጻር ደንብና  ህግ ግምት ገብቶ ደንብ ሳይዘጋጅ  ምንም አይደለም እየተባሉ የተጀመሩ ቤተክርስቲያናት መደርጀት ሲጀምሩ በሚፈጠሩ መንፈሳዊነት የጎደለው የካህናትና ምዕመናን አመለካከትና እለመግባባት በየቦታው ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያኖች  ፡ ለወደፊት የቤተክርስቲያንዋ ህልውና ፈታኝ ክስተቶች ስንመለከት፡ 

1.                                 

·       አመራር እንዲስተካከል የሚነሱ ችግሮችን እንደመንፈሳዊ  በሰላም  በመጨረስ ፋንታ በየፍርድ ቤት ተካሶ ከምዕመናን የተሰበሰበ ገንዘብን ቤተክርስቲያናቱ ያለባቸውን ስንት ችግርና  በሃገር ያልብንን ውጥረት ዘንግቶ ለቤተ ክርስቲያንዋ እድገት እንዳይውል ለጠበቃ ሲሳይ መዳረግ፣

·       ለእም ነት ማስፋፋት ሳይሆን ከሃገር ባስወጣን  እልህ ፡ ለመቻቻል በመጣር ፋንታና የግል ቤተክርስቲያን እንዲኖር ተለይቶ በትልቅ ራዕይ ዘላቂነት ያላቸውን በእቅድ በመክፈት ፋንታ ትናንሽ ቤተክርስቲያናት በየስርቻው እንዴት ተከፍተው እንዴት እንደሚዘጉ የማይታወቁ  ምእመናን የሚወዷቸውን ታቦት ስም በመያዝ በየስርቻው የእገሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እዚህ ተከፈተ ምእመናን ካላቸው የታቦት ፍቅር ይሄዳሉ፣ ወዲያው ቤተክርስቲያን እንግዛ ገንዘብ ስብሰባ፣ ወዲያው ተካሰው ተዘጋ የሚለው ክስተት በመላው ዓለም ለቤተክርስቲያንዋ እድገት ታላቅ ተስፋ የሚሆኑትን ስርዓትንና ቀኖና መሸርሸር ምክኛት ምዕመናን ከአምላካቸው ጋር በፍቅር ለመነጋገር፡ ሰላም ለማግኘት የሚሄድበትን ቦታ በአካባቢው ላለመድረስ ዕርም በቤቴ እጸልያለሁ እያሉ መቅረትና ወደ ግብጽና ደሌሎች ቤተክርስቲያን መሄድ መጀመራቸው     

·        በውጭ ተወልደው ቤተክርስቲያን በመምጣት ያሉ ልጆች ይህን ክስተት ሲመለከቱ በሚያዩት ጸብ ፈጽመው እየተደናገሩ ከቤተክርስቲያንዋ እንዲርቁና ፥ የተገነቡት ቤተክርስቲያናት ተረካቢ አልባ እየሆኑ እንደሌሎቹ  ተከታዮች እንዲያጡና እንደሚዘጉ የሚያደርግ ።  

 መፍትሔው ምንድነው? ምዕመናን ምን እናድርግ?? 

በዓለማችን ታላላቅና ጥንታዊ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት ዛሬ ያሉበትን ሁኔታ በጥቂቱ ስንመለከት፣ 

         ·        እነቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጳውሎስ ያስተማሩባቸው በዮሐንስ ራዕይ በምዕራፍ 2 ና 3 የተጠቀሱት 7ቱ የመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ቤተ                      ክርስቲያናት ከተሞች (ኤፌሶን ፣ ስምርኔስ ፣ ጴርጋሞን ፣ ትያጥሮን ፣ ስርዴስ ፣ ፊላደልፊያና ሎድቅያ) ዛሬ የክርስቲያኖች ቁጥር ከግማሽ                   ሚሊዮን በታች እጅግ አንሶ በዛሬዩቱ ቱርክ ቦታና መብትም የላቸውም። 

           ·        ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትናን ከጥቃት አውጥጥጥጥቶ ሕጋዊ እምነት ያደረገው ታላቁ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ከጣዖት አምልኮ ነጻ የሆነግ አዲስ 

              ንጹህ ከተማ ብሎ የቆረቆራት የኮንስታንቲኖፕል ከተማ ዛሬ ስሟ ኢስታንቡል ተብላ የክርስቲያን ዝናዋ ሲወድም ሃጌ ሶፍያ ብሎ በወርቅ                    ያሰራት ልዩ ቤተክርስቲያን በኦቶማን ቱርክ የ1453 ዓመተ ምህረት ድል ፣ ወርቋ ተዘርፎ ወደመስጊድነት ተቀይራ ስትኖር ቆይታ በ1935 ወደ 

               ሙዚየምነት ተቀይራ በሁሉም ክርስቲያን ስትጎበኝ ኖራ በአሁኑ መሪ ኤርዶጋን በ2020 ዓመተ ምህረት በድጋሚ ወደ መስጊድነት ብመቀየሯ

               በሙዚየምነት እንኳን በክርስቲያኖች መጎብኝቷን አስቀርቷል 

             ·        ከአራቱ መንበሮች አንዱ የነበረው የቅዱስ ማርቆስ መንበር ይገኝባት የነበረችው የግብፅዋ አሌግዛንድርያ በዓለም የነበራት ከፍታዋ ተንዶ                     ጥቂት ክርስቲያኖች ሲቀሩ ፣ እነሱም አዲስ ቤተክርስቲያን የመስራት ፣ ነባሮችንም ማደስና በመንግስት ስራዎች ለመካተት እንዳይችሉ                         ከፍተኛ  ተጽዕኖ ይደረግባቸዋል።

              ·        የቅዱስ ጳውሎስ የስብከት መጀመሪያው ደማስቆ የሚገኝባት ሶርያ ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያኖትችና ቅርስ የነበረባት አሌፖ ከተማ                            ክ2011 አመተ ምህረት ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት ስትወድም ዓለም እያያቸው አላዳናቸውም። ተመናምነው የነበሩት የኦርቶዶክስ                            አማኞች ጭራሹን ተመናምነው ሲሰደዱ ፣ ዛሬ በአጠቃላይ የሃገሪቱ ሕዝብ ላይም አሳዛኝ ጉዳት ደርሷል። ከጦርነቱ በፊት በሶርያ                             ከነበረው ሕዝብ አብዛኛው ከጦርነቱ በፊት በነበረው  ቤቱ አይኖርም፣  በሃገሩ ውስጥ ተፈናቃይ ሆኗል ። ብዙዎች መሰደዳቸውና                           በንብረት ላይ የደረሰው ዘግናኝ የውድመት ሰቆቃ ጆሮ ላለው ትልቅ ደወል ነው። በግልጽ ክርስቲያኖች ሲታረዱ ፣ ሲፈናቀሉ                                 ከተማቸው እንዳለ በእሳት ጋይቶ ሲወድም መላው ዓለምም የእርሱ ፍላጎት ከሌለበት ሃገሮች ሲወድሙ በሕዝብ ላይ ሰቆቃ ሲፈጸም                         አያየም አያይም። እየሰማም አልሰማም ። እንደሩዋንዳ ወደፊት የፌዝ ይቅርታ ይል ይሆናል። 

                   ·        አንድ የነበረችው የጥንቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በ451 ዓመተ ምህረት በተካሄደው አራተኛው የኬልቄዶን ጉባኤ ስትከፈል                             የጥንቱን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አንቀይርም ያሉት / ኦሪዬንታል ኦርቶዶክስ በመባል የሚታወቁት 6

ከሃዋርያው ጴጥሮስ ጀምሮ ለ300 ዓመታት ንጉስ ቁስጠንጢኖስ ክርስትናን ሕጋዊ  ሃይማኖት ነው ብሎ እስካወጀበት ጊዜ ድረስ ክርስቲያኖች በፈተናቸው ሁሉ አንድ ነበሩ። ልክ ነጻንታቸውን ሲያገኙ እርስ በርሳቸው የፈጠሩት ጠብና ጥል በጦርነት አሽንፎ አንድ ያደረገው የሮማን ግዛቱን የሚበታትንበት ስለሆነበት፥  የኒቅያን ጉባኤ በመጥራት 318 የሚሆኑ የዓለም አብያተ ክርስቲያኖች ጳጳሳትን ሰብስቦ ጉባኤውን በመምራት ክርስትናን መልክ ለማስያዝና  የኒቅያ ክሪድ የሚባለውን መመሪያ ለማስጸደቅ ችሎ እስከአሁንም የክርስትና ደርዝ ያለው የሃይማኖት እምነት መሰረት ጥሎ ሁሉም የሚመራበት አርጓል።

 የቤተክርስቲያናችን አባቶች መለያየት ብዙሃኑን የሃይማኖት አባቶች ጳጳሳት፡ ካህናት፡ዲያቆናት፡ መነኮሳት፡ መምህራን ፡ ምዕመናን ፡በጓዳ እያለቀስን እያወራን በመቀመጣችን ዛሬ የኢትዮ ጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደረሰችበትንና  ክብሯ እያቆለቆለ፡መቀለጃና፡ማፈሪያ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው። ክርስትና የጌታን ፈለግ ተከትሎ 120 ሆነው የጀመሩት ሲያድግ ፣ሰብሳቢ፣ አንድ ዓይነት ዕምነት ለማኪያሄድ የሚያስችል መሪ የግድ በመሆኑ የአካባቢ፡ የሃገር፡የዓለም አብያተ ካውንስል ተቃቁሞ ክርስቲያኖች የሚመሩበት እንድ ዓይነት የዕምነት መመሪያ ወጥቶ ሁሉም ያንን ተከትሎ በአንድ የክርስትና ቀኖና ይመራል።የኢትዮጵያ ሲኖዶስም በተቋቋመበት ዓላማና ተግባር መሰረት ክርስትናችን እንዳይዛባ በአንድ ዓይነት ህግ ለመምራት ባለመቻሉ ህልውናዋን በየመልኩ የሚፈትናት የካንሰር ሰንኮፍ መላ ሰውነቷን ወርሮ እየበላት ስለሆነ አፋጣኝ መፍትሄ ከሌለ፡ ከብዙ ጠላቶቿ ጋር አብሮ ሊገድላት ይችላል።ምክንያቱም፦

·       የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ወደሚሞቱበት ያለፍርሃት ሞተው ያቆዩንን ክርስትና ዛሬ የቤተክርስቲያናችንን ጥፋት ዓይቶ  እንደ ንጉስ ቁስጠንጢኖስ የሚገስጽ  መሪ የለም፡፡

·       ዳኝነትም ሆነ ሽምግልና አንድ ወገንን ማስኮረፉ አይቀርም። ነገር ግን ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ለሃዋርያው ጴጥሮስ በጎቼን ጠብቅ ብሎ የሰጠውን ቁልፍና አንተ ዓለት ነህ በዚህ ቤተክርስቲያኔን ትመሰርታለህ ብሎ፥ ጌታው ሞቶ የሰጠውን ክርስትና ቃል አክብሮ በሮማ አደባባይ ተሰቅሎ የመሰረታትንና ተከታዮቹም  ለ300 ዓመት ሞተው የተመሰረተችውን ቤተ ክርስቲያናችንን አንድ አድርገው እንዲመሩና  መንጋቸውን ለመጠበቅ የተመረጡ ብጹዓን አባቶቻንን  ሌሊት በጸሎት  ሲነቁ  እየሆነ ያለውን  ሰደድ  እሳት  አይተው በቆራጥነት  እስከሞትም  ቢሆን ቤተክርስቲያናችንን አንድ ለማድረግ ካልተነሱ እነሱን ለማስታረቅ ማንም አይችልም።

o   ሺህ ገዳይ ቢሆንም ሳዖል በጊዜው ዳዊት የኛ ንጉስ ዕልፍ ገዳይ ነው” መጽሃፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 18፡ቁ 7፡8 ብለው ዳዊትን ሲያሞገሱ ንጉስ ሳዖል  ሰለሰማ ዕልፍ በምትለዋ ቃል ሊገድለው ጦር ይዞ የመጣውን ንጉስ ሳዖልን ፡ ባለበት በዋሻው በእጁ ላይ መጥቶለት  ሊገድለው ሲችል ምህረት አርጎ ፣ ልዑል ጌታዬ ብሎ ለምህረት ለፍቅር እንደቆመ ፡መጽሃፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 24 ቂጥር 2 እስከ 22። እናንተም በሃገርና በውጭ ያላችሁ ብጹዓን  አባቶቻችን ምድራዊ  ሃይልን  ሳትፈሩ  እራሳችሁ  የአንድነት  መረዋ ደወል ብታሰሙ 40 ሚሊዮን ምዕመን ከናንተ ጋር ቆሞ ቅዱሳን ብሎ ለዘለዓለም የሚዘክራችሁ ይሆናልና ፣ እናንተው አባቶቻችንን  ሃሳቡን  በመደገፍ በመነኩሴ መድረክ የሰላም መልእከት እንድታሰሙን  መላ ምእመናን በዚህ ጌታ ጾሞ ፍቅሩን ባሳየበት፣ ጥላቻንና ቂምን ቀብሮ የፍቅር ቀንዲል ሰጥቶ  እንድታገለግሉት  በሰጣችሁ  ሃላፊነትና አባትነት ዘመናችሁ ሳያልቅ አንድ  የምትወዷት ቤተ ክርስቲያን  አንድ እንድታደርጉ በአክብሮት የምእመናን ድምጽ በማሰማት፥ እንማጸናለን፡

በዚሁ አንጻር ደግሞ

§  አባቶቻችንን ወደሰላም በመምጣት ቤተ ክርስቲያናችን ወደ ሰላም እንድትመለስ አባቶች ወደ አንድነት እንዲመጡ ብዙ አዋቂ የሆናችሁ ጳጳሳት፡ካህናት፡ ሰባክያን፡ የቤተክርስቲያን አባቶች ፡ ምዕመናን ፣ጨዋነት የተመላበት የሰላም ሃሳብን በመነኩሴ መድረክ በመጠቀም ጥረታችሁን ባለማሰለስ እንድትቀጥሉ፣

§  40 ሚሊዮን እንሆናለን ተብለን የምንገመተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ  ምዕመናን የስም አማኝ በመሆን ቤተክርስቲያናችን ስትጠፋ እየተመለከትን በሁዋላ ስናጣት ምን ያህል ለራሳችንና ለልጆቻችን፡ ለማንነታችን መለያ በማጣት የሚደርስብንን ውርደት ተገንዝበን በምንችለው ሁሉ በገንዘብ ወይም፡በዕውቀት ወይም በጉልበት ወይም በሃሳብ ድርሻ ብናበረክት 40 ሚሊዮን የሚለካ ሃይል ይኖራል ማለት ነው። 

§   ሁላችንም በአንድ በቁርጠኝነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠን የፍቅር መንፈስ በመቆም ቤተክርስቲያናችን መንግስት በተቀየረ ቁጥር በየጊዜው የምትፈራርስ እንዳትሆን የቤተክርስቲያናችንን ልእልና ለማስከበር እንድ ላይ እንድንቆምና ቤተክርስትያናችን በየትም አገር እንደካቶሊክ ከአንድ ቢለዮን በላይ በተለያዩ  አገሮች ያሉ አማኞች ሁሉ ደንባቸውን ጠብቀው በየስርቻው ሳይከፋፈሉ እንደሚተዳደሩ፡ የኛም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመከፋፈል እንዳትዳከም በአንድ ስርዓት እንድትመራ ለማድረግ ይረዳል በማለት ይህን የመነኩሴ ድህረ www.menekuse.org ወይምwww.melekuse.org በሁለቱም መጠቀም ይቻላል የማንም የግል ሳይሆን  ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች መንፈሳዊ  መድረክ እንዲሆን የተዘጋጀ በመሆኑ ሁላችንም በመድረኩ መንፈሳዊና  ሰላማዊ ውይይት በማድረግ  መፍትሄ እድናመጣ በትህትና እንጠይቃለን። 

  የቤተክርስቲያንትዋን ህልውና ፈተኝ የመለያየት ክስተት እንዲወገድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በጎልጎታ ያፈሰሰውን ደም ፡ እነቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ የከፈሉትን መስዋዕትነትና ሌሎች ክርስቲያኖች ከ300 ዓመት በላይ የሞቱበትን ክርስቲያናዊ ዓርዓያነት በመውሰድ ሁሉም አባቶች በህይወት እያሉ ወደሰላም እንዲመጡ ሁላችንም የድርሻችንን እንድናደርግ የፍቅር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ፡ የአማላጅ እናታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት፡ የቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት፡ የሰማዕታትና ፡ቅዱሳን ጸሎት ከኛ ጋር  እንዲሆን በማሳሰብ፣ ይህ የመነኩሴ ድህረ ገጽ www.menekuse.org/

በገዳም የተሰየመው _ መነኮሳት የሚኖሩበት ገዳም የጸሎት የሰላም ቦታ እንደመሆኑ በመነኩሴ ድህረ ገጽም ሰላም በሰፈነበት መንፈስ በመከባበር ፣ ቤተክርስቲያናችንን አንድ በማድረግ የሚፈራርሱት ቤተክርስቲያኖቻችን እንዲገነቡ፣ እምነታችን ሳይዳከም እየተስፋፋ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ፣ መንፈሳዊ ተግባር እንዲያድግ፣ ደረጃዋ  ከመሰል አብያተ ክርስቲያን እኩል እንዲሆን በመሆኑ፣ ዘለፋ ወይም ስድብ በመላክ የአምባጓሮ መድረክ እንዳይሆን ፣ ሰላማዊ የውይይት ሃሳቦች ብቻ ማቅረቢያና የትልቅ ተግባር መትለሚያ እንዲሆን  ሁሉም እንዲሳተፍና እንዲተባበር  የመነኩሴ ድህረ ገጽ  አዘጋጆች በታላቅ መንፈሳዊ ትህትና እናሳስባለን።

Tabs

The Bermuda Triangle holds a different definition in each of our minds. It’s a vortex of wild weather, a mysterious energy field, or simply a remote place to dramatize the sinking of ships from centuries past. In truth, no single answer exists. Rather it is a collection of various forces at work, much like the many aspects of life.

ኢትዮጵያውያን በኢየሩሳሌም ያላቸው ክብር ገላጭ እንዲሆን የተሰየመው ኢትዮጵያ መንገድ

To fully see the reality of plastic pollution in our oceans, it may help to recap how it all begins. Plastic is made from crude oil using a procedure that affects the carbon in the oil.

To fully see the reality of plastic pollution in our oceans, it may help to recap how it all begins. Plastic is made from crude oil using a procedure that affects the carbon in the oil.

የፋና እሳቤ

በቅዱስ ማቲዎስ  ምዕራፍ 5 ክቁ 13 -16 ጊታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ እናንት ጨው ናችሁ። ውሃውን ዓለም አጣፍጡ ፣ የዓለም  ብርሃናችሁ የጨለመን ሁሉ አብሩ፣ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልተሰወር አይቻላትም ። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።” እንዳለን የተረጂና ተረጂ ሳይሆን ሁሉም በተሰጠው ጸጋ በአንድ ጨለማ ክፍል ፣ አንድ  የመብራት አምፖልና አምፖሉን በሚያበራ ሰው ትብብር ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ   ምዕመናንና ቤተክርስቲያን ተጣምረው ፋና እንዲሆኑ የሚያስችል ኦርቶዶክሳዊ  የበጎ ተግባር እሳቤ ነው። 

ፋና ለምን? እንዴት 
⦁     ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር  89/90 ቁ 10” የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ፡ ዓመት ፡ ቢበረታም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው። ከእኛ ቶሎ ያልፋልና” ሁላችንም ሰባና ስማኛአ ስንደርስ የነበረን እውቀት ባዲስ ተተክቶ እርዳታ ፈላጊ እንሆናለን 
⦁     በጥበብና ሃብት የከበረው ንጉስ ሰሎሞን በመጽሃፈ መክብብ ምዕራፍ 3 ቁጥር 12 “ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ” ባለን ጊዜ እኛው ለበጎ ካላዋልነው የሰሰትለትን ሁሉ  ማን እንደሚወስደው ሳናውቅ ጥለነው እንሄዳለን።
ና እንዴት? በምን?  

ፋና ድርጅት በማቋቋም ገንዘብ ሰብስቦ የሚሰራ አይደለም፣ ፋና በጽኑ እምነት በግል አነሳሽነት በዓቅም የተዳከመ ቤተ ክርስቲያንንና የምዕመናን ህይወት ቀያሪ ስራ  በመስራት አርዓያ መሆን ነው። ይህንንም በሌላ ቦታ ሞክረን ጥሩ ውጤት አስገኝቷል። ካለን ጸጋ  ጋት የሚያክል በመቆንጠር ብዙ መስራት ስለሚቻል ፋና በኢትዮጋት ተብሏል።   ጋት ማለት ከአባቶች መለኪያ  ትልቁ  ክንድ ፣ ከዚያም ስንዝር፣ አነስተኛው ጋት ነው።  (ጋት ማለት  የአራት ጣቶች  ስፋት ያህል ) የበረታ ክንድ ፣ ስንዝር ሁሉም   ጋት  እንዲሰጥ የሚጣራ ኦሮቶዶክሳዊ  የተግባር ተሳትፎ ማለት ነው። 

ፋና በኢትዮጋት የገንዘብ  ምንጮች  

ከብክነት ጥቂት ልገሳንና  ያሉንን ትርፍ ነገሮችን አስቦ ለሌላቸው መስጠት  ከደስታ ዝግጅቶች፣    ልጅ ሲወለድ  ፣ ከክርስትና ፣ ከልደት፣  ከምርቃት ፣ ከሰርግ ፣ ሹመት ፣ ዝክር ድግሶች ትንሽ መታስቢያ፣ በጎ ስራ አስቦ መቆንጠር ነው    

3  ከሃዘን ወቅት ዝግጅቶ፣   ሃዘንን በለቅሶ በተዝካርና ትልቅ ሃውልት ብቻ በመገንባት ሳይወሰን  አስፈላጊውን  ዝግጅት በመጠኑ  አድርጎ ለሟች ዘለዓለማዊ ማስታወሻ የሚሆን  ቋሚ  ለመታሰቢያ መስራት ልምድ ማዳበር ነው።

አንድ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት “እኛ መነነኮሳት በገዳም ብንኖርም ስራችን ለዓለም ለመፀለይ ነው ። እዚህ ገዳም ተቀምጠን ከዓለም የማንወጣ እንዳለን ሁሉ ከተማ ተቀምጠው የመነኩሴ ተግባር በሚያከናውኑ የጸኑ ክርስቲያኖች አገልግሎት ስለሆነ ገዳማትና ቤተክርስቲያን የሚጠበቁት በዓለም ውስጥ ሆነው በፍቅር ሰርተውና በእምነት ጸንተው ቤተክርስቲያንን የሚያጠ ናክሩ አገልጋይ ምዕመናኖች ሁሉ መነኩሴ ናችው” ብለዋል።  ሁላችንም በዚህ በፋና ጉዞ ከተሳተፍን ሁላችንም መነኩሴዎች ነን።

Table

Tewahido Church Church Directory Bible Video
       
light

$ 20 per month
  • Photographs
  • tells stories
  • links
  • specific topics
order now

Plus

$ 30 per month
  • multi-author
  • links
  • specific topic
  • photographs
order now

   ዛሬ  በአብዛኛው የምዕራቡ ዓለም ቤተ ክርስቲያናት  እየተዘጉ፡ አማኝና አምልኮተ እግዚአብሄር የሚፈጽም  በመጥፋቱ፡ ወደ ንግድ ቤት እየተለወጡ  ባለበት ዘመን ብዙዎቹ ቤተክርስቲያናት በኢትዮ ጵያ ኦርቶዶክስ ዓማኞች  እየተገዙ ፡አዲሶችም  እየተገነቡ ናቸው።

·       በልዩ ስርዓት የሚቀርበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ  ጸሎት በመላው ዓለም እየፈሰሰ  ፣ ታቦተ ሕግ በፖሊስ ሞተር እየታጀበ በታላላቅ የአሜሪካ፡ አውሮፓና  ካናዳ  ከተሞች ጥምቀት  እየተከበረ ፣ ይገኛል።

·       ዓለም ትክክለኛው አምላክ ለሙሴና አሮን ባዘዘው ክብር የተላበሰ እምልኮትን በማየታቸው ብዙዎች ይህ ነው አምልኮተ እግዚአብሄር እያሉ እየተጠመቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታይ እየሆኑ ናቸው።

·       ሃብትና ገንዘብ ይዞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ቤተክርስቲያን እናስፋፋ ተብሎ መንግስት ወይም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ቢጠይቅ አንድም ቤተ ክርስቲያን ተፈቅዶ ለመስራት አይቻልም ነበር ። አሁን ግን በንቂያው የኦርቶዶክስ የአምልኮት ስርዓት መሰረት የተመሰረተችውና ልዩ የራስዋ የቅዳሴ ስርዓተ አገልግሎት ለመላው ዓለም እንዲታወቅ እምላክ የፈቀደው ነው ለማለት በሚያስችል ግንዛቤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ቅዳሴ በሃያልዋ አሜሪካ ባሉ በመላው 50 ስቴቶች ከተሞችና፡ መላው ዓለም  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተክርስትያን  ግንባታ እያበበ ነው። 

Progress Bars

Counters

1980
since
18000

Happy Believers!

1180
likes