የመነኩሴ ጽንስ ሃሳብ

 

 

www.menekuse.org

     መነኩሴ ጠቅላላ ህይወቱን ለእግዚአብሄር የሰጠ ፡ በፈቃደኝነት እራሱን ደሃ በማድረግ ለምንም ዓለማዊ ኑሮ ፡ ገንዘብ ፡ ምቾትና የግል ጥቅም ሳይደለል ለዓለም ሁሉ ሰላም በመጸለይ ለበጎ ስራ ቃል ኪዳን የገባ በሁሉም የታመነ የቤተክርስቲያን ቅን አገልጋይ ማለት ነው። አንድ ታላቅ የሃይማኖት አባት ሲያስተምሩ "በዓለም ውስጥ ሆነው በፍቅር ሰርተውና በእምነት ጸንተው ቤተክርስቲያንና ገዳማትን የሚያጠናክሩ ሁሉ መነኩሴዎች ናቸው" እንዳሉት ፣ የመነኩሴም ጽንሰ ሃሳብ የተወለደው የነዚህን መነኩሴዎችና የጸኑ አማኞች  የበጎ ስራ ጽናትና ራዕይ በመከተል በቀና መንፈስ ህብረተሰብን በማነቃቃት ፣ ከቤተክርስቲያን ጎን ተሰልፎ ያለውን ዕውቀትና ገንዘብ በማካፈል ፣  በኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ቤተክርስቲያናችንን ለመጠበቅና ለማሳደግ ፣ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ገዳሞቻችንን ህጋዊ መብት አስከብሮ ለመንከባከብ ፣ በቀረው ዓለም በማበብ ላይ  የሚገኙት አብያተ ክርስቲያኖቻችን በየቦታው ያልተሟሉ ትንንሽ ቤተክርስቲያናት ከመክፈት ተላቀው በትልቅ ራዕይ ለሃገር ጭምር የሚተርፉ፣ በፍቅርና በሰላም እምነትን በማስፋፋትና ለትውልድ ጠቃሚ ተግባሮችን በመስራት በመንፈሳዊ የዳበሩ ለሰው ልጆች ማፍሪያ ማድረግ ነው። የቤተ ክህነት መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከ40 ሚሊዮን ያላነሱ  ምዕመናን ፡ 400 ሺህ ካህናትና 1000 ገዳማት ባለቤት እንደመሆንዋ፣  ሁሉም ተከታይዋ ከዳር ሳይቆም በአንድነት ደግፎ ከተሳተፈ  ቤተክርስቲያናችን ያለጥርጥር ፣ በየጊዜው የሚፈትኗትን ክፉ መንፈሶች ተቋቁማ ፣ ሳትከፋፈል የነበራት አንድነት ተመልሶ እንደጥንቱ በአንድነት ፣ በፍቅርና በሰላም እምላክን የምናመሰግንባት ፣ በመንፈስ በልጽገን ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ለመወረስ የምንችልባትና፣ በሰላም እንድንኖር የምትመራን እንድትሆን በማሰብ ይህንን የመነኩሴ ድህረ ገጽ www.menekuse.org  በመጀመር ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ በየዓምዱ በቀረቡት ሃሳቦችና ሌሎችንም በመጨመር  ባለው የሙያ ችሎታና አቅም በመሳተፍ ፣ ከሚያመልክበት የአጥቢያው ቤተክርስቲያን በተጨማሪ ቢያንስ አንድ ቤተክርስቲያን ለመርዳት  "በኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት /ORTHODOX MISSIONARY SERVICE/  እንድንሳተፍ በቁርጠኝነት በመነሳት ፣ አቅም ያለው ከቻለ በግል ፣  ወይም በቤተሰብ ፣ በጉዋደኛ ካለው ፀጋ ጋት ያህል በመቆንጠር  ለቤተክርስቲያናችን ህልውና አስተዋጽኦ እንድናደርግ ቆራጥ መንፈሳዊ ጥሪ ነው። 

          ይህም ከዳር እንዲደርስልን ፣ የፍቅር አምላክ የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ፡ የአማላጅ እናቱ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም፡ ልመና ፡የተራዳኢ መላእክትና የጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት ተሳክቶ ለቤተክርስቲያናችን ዘላለማዊ እንድነት እንድናመጣ ይርዳን። አሜን!!!!!!!!!!!

 

A Bit of Background 

Menekuse is the Amharic word for a monk. A Menekuse is an individual who is totally dedicated to God, takes the vows of poverty, chastity and obedience. They serve the church with dedication, work for the salvation of the world, and give their lives to charity work. The vision of Menekuse is born out of the lives of these dedicated Menekuses. Our vision is to empower communities by partnering churches, imparting vision to the next generation and bring together people to preserve the Ethiopian Orthodox Tewahedo Churches in Ethiopia,  our monasteries in Jerusalem and our booming churches all over the world. 

 

 

 

 

 

 

 

                                                                                                                                                                                                                  

 

          

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

If you are a professional please join us to help something in some way.

 

 

  

If you are a professional please join us to help something in some way.

 

God Bless You All.

Melekuse Team

Info@melekuse.org