በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት

                                                    

     ይህ ከላይ መላው የዓለም ህዝብ ዙሪያውን ከቦ ገብቶ ለመዳሰስና ለመባረክ የሚታገልበት በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ጎልጎታ ውስጥ የሚገኘው እኛን ከሃጡያት ከሲኦል ለማጣት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ፣ ተቀብሮ፣ ሞትን ድል ነስቶ የተነሳበት የመቃብሩ ቦታ ነው። ይህን በመሰለ ፍቅር ስለኛ ተሰውቶ ዲያቢሎስን ድል የነሳበትን ቦታ በስሙ ክርስቲያኖች የተሰኘነው ሁሉ በቦታው ተገኝተን ለመሳለምና ለመባረክ ያብቃችሁ እንላለን። የሱን መስቀል ተሸክመን ክርስቲያን ተብለን የተጠራን በሙሉ ይህን ፍቃሩን እያሰብን ሰባ ጊዜ ሰባት 490 ጊዜ የወንድምና እህቶችን በደል ይቅር በሉ ብሎ የሰጠንን የፍቅር ቃል እያሰብን ሁላችንም በፍቅርና በሰላም እንድንኖርና  እንድንዋደድ በፍቅሩ ይዳብሰን።

አሜን!!!!!!!!!!!! መነኩሴ!!!!!!!!!!! መነኩሴ!!!!!!!!! አሜን!!!!!!!!!! መነኩሴ !!!!አሜን  

 

 

 

ይህ በጎልጎታ ከጌታችን መቃብር አጠገብ ተያይዞ የሚገኘው የዴር  ሡልጣን መድሃኔዓለም የኢትዮጵያ ገዳም ነው 

 

 

 ኢትዮጵያ ከሙሴ ጀምሮ አምልኮተ እግዚአብሄር የሚታወቅባትና ሰሟም በቅዱስ መጽሃፍ በየቦታው የተጠቀሰ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያውያንና ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ግንኙነት ከብሉይ ኪዳን እስከዛሬም ያልተቆረጠ ሲሆን  ይህም በብዙ ታሪክ ዘጋቢዎች ፡ ጽሁፎች ፣ ተረጋግጧል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በእስራኤል አገር ሰባት ገዳማት ይዛ መገኘት ለዚህ ምስክር ነው።

 

የገዳማቱ ዝርዝር:

1.    ዴር ሱልጣን ገዳም በ320 ዓ ም/ በአሮጌው ከተማ ውስጥ በጌታ መቃብር አጠገብ/

2.    ደብረ ገነት ገዳም በ1850ዓ ም ተመስርቶ / በኢየሩሳሌም ከተማ የሚገኝ/

3.    ቅዱስ ፊሊጶስ ገዳም በ 1883  ዓ ም /ኢየሩሳሌም ከተማ /

4.    ቅድስት ሥላሴ ገዳም በ1915 ዓም /ዮርዳኖስ ወንዝ አሁን ኢያሪኮ ድርብ/

5.    ቅዲስ ገብርኤል ገዳም በ1920 ዓ  ም/ ኢያሪኮ ከተማ/

6.   ምስካነ ቅዱሳን ዓልዓዛር ገዳም በ1945 ዓ ም/ ቤታንያ/

7.    ቤተልሄም ገዳም በ1982 ዓ ም/ ቤተልሄም/ 

እነዚህም ገዳማት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓማኞች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ኢትዮጵያዊና ለመላው ጥቁር ሕዝብ ጭምር ኩራት በመሆናቸው፣ የገዳማቱ ታሪክ ይዘት እንዲጠበቅ ሁሉም ባለው ዓቅምና ሙያ  ሊሳተፍ ይገባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካሏት 7 ገዳማት ውስጥ 6ቱ በገዳሙ መነኮሳት ማህበር ቁጥጥር ስር በመሆናቸው ሁሉም ከተባበረ የሚፈለገውን የማሻሻል ስራ ማከናወን ይቻላል።

ዋናውና አንገብጋቢው ግን ጌታ በተቀበረበት በጎልጎታ ለረጅም ጊዜ በዙ ያለም መረጃዎች እንደሚያረጋግቱት እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በዋናው ጎልጎታ ውስጥ የነበሩን እራት መቅደሶች ተወስደው የቀረንም አንዱ ይዞታችን በአንደኛ ተራ ቂጥር የተጠቀሰው የዴር ሡልጣን ገዳም  በመባል የሚታወቀው ነው።የዴር ሡልጣን ገዳማችን ያለበትን ውጣ ውረድ ሕዝብ ሊያውቀውና ሊሳተፍ ባለመቻሉ ዓቅማችን ደካማ በሆነበት ጊዜ በግፍ ከመነጠቃችንም በላይ  ከንጭራሱ ከዚያ ደብዛችን እንዲጠፋ የማያቋርጥ ተጽዕኖ  ቁልፉን በያዙት ግብጾች ከፍተኛ ተጽዕኖ በመነኮሳቱ ላይ በመደረግ ላይ መሆኑ ነው።

የዴር ሡልጣንን  ገዳም በሚመለከት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጽህፈት ቤት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር  2000  ዓ ም የተዘጋጀው ጸሁፍ የገዳሙን ታሪኩንና ችግሩን ያካተተ በመሆኑ ጽሁፉን እንዳለ ኢትዮጵያውንን ለማሳወቅ ሰለሚረዳ ከዘህ በታች ሙሉውን እንዳለ ብ አቅርበነዋል።

“ደብረ ሥልጣን (ዴር ሡልጣን)

ዴር ሡልጣን ፦ሥያሜው በግዕዝ ደብረ ሥልጣን ፥ በዓረብኛ ሡልጣን ሲሆን ይህ ገዳም የሚገኘው ከጌታ ቅዱስ መቃብር ቤተመቀደስ በስተምስራቅ ከቅድስት ዕሌኒ ቤተመቅደስ በላይ ነው።ዴር ሡልጣን ማለት የንጉሥ/የመሪ/ገዳም” ማለት ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ትርጓሜ ሥያሜውን ያገኘው ቦታው ጥንቱንም ንጉስ ሰሎሞን ከኢትዮጵያ ለበዓላት ለሚመጡ መንገደኞችና መልዕክተኞች ማረፊያ እንዲሆን ለንግስት ሳባ የሰጣት በመሆኑና ኋላም በክርስትናው ዘመን ገዳም ተመሥርቶበት በኢትዮጵያውን ነገስታት ሲረዳ የኖረ መሆኑ ነው።

1.     ሰረታዊ ታሪክ ፦

ኢትዮጵያውያንና የቅድስት ሀገር ትውውቅ እስከ ብሉይ ኪዳን ይዘልቃል።

·       ክርስቶስ ልደት በፊት ዝነኛው የንግሥተ ሳባና የንጉስ ሰሎሞን የኢየሩሳሌም ግንኝነትነው /1ኛ ነገ 10፡1᎗13/።

·       በሐዲስ ኪዳን ያለው ትውውቅ የመጀመሪያው ደግሞ ከጌታ ልደት በኋላ ትንቢተ ኢሳይያስን እያነበበ በሠረገላው ሲጓዝ ቅዱስ ፊልጶስ በመንፈስ ተልኮ ያስተማረውና ያጠመቀው ኢትዮጵያዊ

ጃንደርባ ታሪክ ነው። / የሐዋ ሥ ም 8፡26/

·       በ380 ዓ ም ሁለቱ የቅዱስ ጀሮም ደቀመዛሙርት ቅድስት ፓውላን ልጇ ቅድስት ኢዮስቶቹም  ሮም ለሚገኙት ሊይታና ማርሴላ ለተባሉት ጓደኞቻቸው ወደ ኢየሩዳሌም መጥታችሁ ኑሩ በማለት በላቲን በጻፉት ሁለት ደብዳቤዎች ላይ በየቀኑ መነኮሳ,ት በቡድን ከህንድ፡ ከፋርስና ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩዳሌም እንደሚደርሱ አመልክተዋል። /ደብዳቤችን መፈለግና ማቅረብ/

·       በ636 ዓ ም ከሊፋ ዑመር ኢብንኧልኸታብ  ኢየሩሳሌምን ከተቆጣጠረ በኋላ ለክርስቲያኖች ,በሰጠው ቃልኪዳን (ኦማራይት ኮብናንት) ላይ “  ,,,, በኢየሩሳሌም ውስጥ ከሚኖሩት ሌሎች ክርስቲያኖችም ማለት ጆርዳናውያን፡ኢትዮጵያውያን(ሀበሾች) እንዲሁም ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም(ለመጎብኘት) የሚመጡ እውሮፓውያን ኮፕቶች (ግብጻውያን)፡ አሶራውያን (ኩርዶች),,,” የመለው  ንባብ የኢትዮጵያውያን ማህበር ከሌሎች ለመሳለም ከሚመጡት አንጻር እንደ ነዋሪ እንደሚታዩ ያረጋግጣል።

በኋላ ዘመንም ቢሆን የኢትዮጵያውያንና የቅድስት አገርን ግንኙነት በተለይም ደግሞ  የያዟቸውን ይዞታዎች በትክክል የሚያሳዩ መረጃዎች በብዙ ተሳላሚዎ ች ጽሁፍ በነገስታት አዋጆችና ሌሎች እንደ ሽሪዓ ፍርድ ቤት ድንጋጌዎች ባሉት ውስጥ ይገኛል።

·       በ786 ዓ ም ዊልባልድ የተባለ ጅርመናዊ ጳጳስ በገሊላ አንድ ኢትዮጵያዊ ተሳላሚ እንዳገኘ አመልክቷል።

·       በ1323 ዓ ም ሁለቱ ፍራንሲስካን መነኮሳት ሲሞና ኹጎ የኢትዮጵያውያንን የቅዳሴ ሥርዓት እንደተሳተፉ ሲገልጹ ይህ ዓይነት ቅዳሴ በጎልጎታ ውስጥ በምትገኘው የቅድስት ማርያም ቤተመቅደስና  በቅዱስ ሚካኤል መቅደስ የሚካኬድ እንደሆነ እንዲሁም 1374 ዓ ም ሂኮሎ ዳ ፖጌቦንሲ የተባለ አባት ገልጻል።

·       ከ27 ዓመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም የመጣው ሊዎናርዶ ፍሪስኮባልዲ ኢትዮጵያውያን አራት መቅደሶች እንዳሏቸውና ከእነዚህም አንዱ የቅዱስ ሚካኤል መቀደስ መሆኑን ሲገልጽ ሌሎች መንገደኞች ለምሳሌ እንደጀርመናዊው ሲባልድ ሬይተርና ጅሃን ተኑድ ያሉት ይኸንኑ ደግመው አረጋግጠዋል።

·       በ1517 ዓ ም በሡልጣን ሳሌም በተሰጠ አዋጅና በ1550 በንጉስ ሱልጣን ሱሌይማን የጸናው የኢትዮጵያውያንን ይዞታ የሚዘረዝር አዋጅ ላይ ስለዴር ሡልጣን እንዲህ ተጽፏል።” በስተደቡብ በኩል የሚከፈተው ታችኛው የኢትዮጵያውያን ቤተመቅደስና በመካነ  መቃብሩ ቤተክርስቲያን የሚገባው የሡልጣን ገዳም (ዴር ሱልጣን ከነቤቶቹና ከነመኖሪያዎቹ የኢትዮጵያውያን ንብረት ነው።”

·       በተጨማሪም በ1530 ዓ ም ፈረንሳዊ ተሳላሚ ዴንስ ፖስት “,,,, አብረሃም ልጁን ይስሃቅን በሰዋበት ቦታ ሀበሾች የሚባሉት ጥቁር ህዝቦች ቤተመቅደስ ይጠብቃሉ፣ በተጨማሪም አብረሃም ልጁን ሲሰዋ ያምር እንደነበር የሚያምር የወይራ እንጨት አለበት፡” በማለት ከነትውፍታዊ መረጃው አረጋግጧል።

·       ከዚህ ሌላ  ፍራንሲስኮ  ቨርኔሮ በ17ኛው መቶ  ክፍለ ዘመን “ ,,,እነርሱ (ኢትዮጵያውያን) ክጌታ ቅዱስ መቃብር ቤት መቅደስ አደባባይ ፊት ለፊት ቤተመቅደስ አላቸው። በዚያም ጥቂት ጠበብ ያሉ ጨለማ ክፍሎች አሉ። በዚያው ባዶ መሬት ላይ ይተኛሉ” ሲል በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በዴር ሱልጣን ያሳለፉትን የተጎሳቆለ ኑሮ አስቀምጧል።

የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት የተከበረ ማህበር እንደነበራቸው ብዙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

·       በ1531ና በ1547 ሁለት የኢየሩሳሌም የሸሪዐ ካውንስል ድንጋጌዎች የሚያሳዩት የኢትዮጵያውያን ማህበር እለቃ ከጥንት ጀምሮ ከግሪክ ፓትርያርክ ሳይቀር ቀድሞ የቅዳሜ ሥዑር ዕለት ከጌታ መቃብር /ጎልጎታ/ ውስጥ ብርሃን ያወጣ እንደነበር ሲያረጋግጥ ፣

·       በሌላ በኩል የኢትዮጵያ  ነገስታት ለምሳሌ አጼ ዐግብዐጽዮን በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እና  አጼ ዘርአያዕቆብ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ መነኮሳት የጻፏቸው ደብዳቤዎች የኢትዮጵያውያን ማህበር ከነገስታቱ በቂ ድጋፍ ይደረግላቸው የነበረ መሆኑን ያሳያል።

·       ይሁን እንጂ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የግራኝ መሐመድ መነሳትና በኋላም የዘመነ መሳፍንት መከሰት ምክንያት ግንኙነቱ በመቋረጡ አንዳንዶቹ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ወደ አውሮፓ ለመሰደድ በቅተዋል። ችግሩን ችለው የታሪክና የቅድስና ቦታቸውን ለመጠበቅ በኢየሩሳሌም የቀሩትም በጎልጎታ ውስጥ ያላቸውን መብት በግፍ ከመነጠቃቸውና በዴር ሡልጣን ከመወሰናቸውም ሌላ ከላይ ፍራንሲስኮ ቭርኖሮ ለገለጸው ዓይነት መራራ  ኑሮ ተዳርገዋል። ይሁን እንጂ ዘመን መሳፍንት አክትሞ  ዘመነ ነገስታት ሲተካ  ለማህበሩ የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል።

መላ ያጣው ክርክር፡

·       1774  ዓ ም የኢትዮጵያ  መነኮሳት ኢብራሂም ጁሃሪ የተባለውን ግብጻዊ ከአገልጋዮቹ ጋር በእንግድነት ያስጠጉታል። ውሎ አድሮ  አለቃ ልሁን ማለት ይገምራል።

·       ይሁን እንጂ እንደ ጳጳስ ሳሙኤል ጎባትና የብሪታንያ ቆንስል ጀምስ ፊን ኮፕቶች በዴር ሡልጣን ላይ ግልጽ የይገባኛል ክርክር ያነሱት በገዳሙ በ1838 ዓ ም ከተከሰተ የተስቦ ወረርሽኝ በኋላ ነው።በዚህ ወረርሽኝ የኢትዮጵያ መነኮሳት በተስቦ ሲያልቁ ኮፕቶች በአርመን  ጳጳስ እርዳታ የዴር ሡልጣንንና የሁለቱን ቤተመቅደሶች ቁልፍ ከተረፉት መነሎሳት እጅ በጉልበት ይነጥቃሉ። ከዚያም በኋላ በማጽዳት ስም ቦታውን ለማቃጠል እንዲፈቀድላቸው  በወቅቱ የኢየሩሳሌም አስተዳዳሪ ክነበረው ግብጻዊ ኢብራሂም ፓሻ ይጠይቃሉ ። በአጋጠማቸው ዕድል ተጠቅመው የኢትዮጵያውያንን ትልቅ ቤተመጻሕፍት ያቃጥላሉ።

·       ከዚህ በኋላ  በባይዛንታይን ዘመን በአብርሃም ገዳም ምክንያት የተነሳውን ክርክር ይዘው ይገባናል በማለት ጥያቄ  ያቀርባሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩት ቱርኮች  በአብርሃም ገዳምና በዴር ሡልጣን መካከል ልዩ ነት እንዳለ አስረድተው በ1846 ዓ ም እምቢ ይሏቸዋል። ቢሆንም ግን በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉት ድርጊቶች የቱር`ክ አስተዳደር ለግብጾች ማድላቱን የተለያዩ  መረጃዎች አመልክተዋል።

·       በ1850 በሳሙኤል ጎባት ምክር የኢትዮጵያውያን የዴር  ሡልጣንን ቁልፍ መልሰው እጅ አደረጉ። በመቀጠል በ1890 ዓ ም ኮፕቶች የሰሚኑን ግድግዳ ለማፍረስ ፈልገው ኢትዮጵያውያኑ መነሎሳት አምርረው በመቃወማቸው የቱርክ መንግስት በይርጋ ደንብ መሰረት አግዷቸዋል።

·       በዚህም ንዴት የሁለቱን መቅደሶች ቁልፎች ለውጠው ዘጉ። እስከ 1870?ዓ ም ለኢትዮጵያውያን ዝግ ሆነው በቆየበትም ወቅት ኢትዮጵያውያን የትንሣኤን በዓል በድንኳን ለማክበር ተገደዱ። ሆኖም አጼ ሚኒልክ በደጃዝማች መሸሻ መሪነት የላኩት የልዑካን ቡድን በሰበሰበው መረጃና  ኋላም በተገኙት መረጃዎች መሰረት ለጆርዳን መንግስት አቤቱታ ቀርቦ ክ8 ዓመት ጥናት በኋላ በ1881 የጆርዳን መንግስት ለኢትዮጵያን ወሰነ። በውሳኔው መሰረት ኢትዮጵያውን መነኮሳት ለ40 ቀን ብቻ ቁልፉን ከያዙ በኋላ በግብጽ መንግስት ጣልቃ ገብነት ውሳኔው ተቀልብሶ ኮፕቶች መረጃ ያቀርባሉ በሚል ሰበብ ቁልፉን እንዲመልሱ ተደረገ።ነገር ግን የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡም ሆን ተጨማሪ መረጃ እንዲያቀርቡ ዕድል ሳይሰጣቸው እስከ 1871 ዓ ም ድረስ ጉዳዩ  ተዘግቶ ቆየ።

·       በ1971 ዓ ም የእስራኤል የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደገና አይቶት ችግሩ እስኪፈታ ድረስ አሁን ባለው መልኩ ኢትዮጵያውያን ገዳሙን እንዲያስተዳድሩ ሲል ወሰነ።ኢትዮጵያውያውያንም የቤተመቅደሶቹን ቁልፎች እጅ እደረጉ።

ኢሰብዓዊነት

ሰብዕና  ትርጉም የሚኖረው ሰው በዓይኑ አይቶ መፍረድ እስከቻለ ድረስ ብቻ ነው። ይህንን ለማለት ያስገደደን ደግሞ እሁን ሰዓት በገዳሙ ውስጥ ያለው ሁኔታ ነው።

·       ከሁለቱ መቅደሶች አንዱ መቅደስ በጣም ትልቅ አደጋ ላይ ያለና  አስቸኳይ ጥገና  የሚያሰፈልገው መሆኑን ማንም በዚያ ያለፈ  ሰው ሊረዳው የሚችለው ነገር ነው ።

·       ሌላው እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ በደጃዘማች መሸሻ የልዑካን ቡድን ባስከፈተው የምስራቅ በር በኩል ያሉት የመነኮሳት መኖሪያ ቤቶች ሁኔታ  ነው። እነዚህ ቤቶች እጅግ በጣም ጠባብና ለአንድ ሰው መኖሪያ የማይበቁ  ብቻ  ሳይሆኑ ምንም ዓይነት ለኑሮ  መሰረታዊ  የሆነ ነገር ለምሳሌ መታጠቢያ  ቤት የሌላቸው ናቸው።

·       በተለያዩ  ጊዜያት የገዳሙ ማህረሰብ መኖሪያ ቤቶቹ በተገቢው ሁኔት እንዲሰሩና  ቤተመቀዶሶቹም እንዲታደሱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምንም ዓይነት አዎንታዊ መልስ ሊያገኝ አልቻለም።

·       በቅድሚያ  የሡልጣን  ሱሌማን አዋጅ ኢትዮጵያውያን ቤተክርስቲያናቸውን እንዳደሱ ሲያስረዳ  “,,,,በኢየሩሳሌም የሚገኘው የኢትዮጵያ  ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያዊው አባ ዮሐንስ ትጋት በ1500 ዓ ም መታደስ ጀመረ። የማደሻውም ገንዘብ ከኢትዮጵያ  መንግስትና  ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ዘንድ የተላከ ነው,,,” ይላል።

·       በአንጻሩ በዴር ሡልጣን ላይ የይገባኛል  ክርክር ከተጀመረ በኋላ ባለቤቱ በትክክል እስኪረጋገጥ መንግስት ኃላፊነቱን ወስዶ ያሳድሰዋል በሚል ምክንያት ኢትዮጵያውያንን ከማደስ አግዷል።

·       ገዳሙ ለረጅም ዘመን ያለእድሳትና  ጥገና  መቆየቱ ለተመልካች ዘንድ ተከታታይ ማጣት ሊመስል ይችላል።ነገር ግን ለኢትዮጵያውያኑ ጥያቄ ተገቢ መልስ ከማጣት እንጂ በዚህ ውስጥ መኖሩ ተመራጭ ሆኖ አይደለም።

·       እንግዲህ በገዳሙ የሚኖሩ አባቶች መብት የተነፈጋቸው  መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። ምክንያቱም ሰውን ወደ በረዶነት በሚለውጥ ክረምትና  እጅግ በሚሞቅ የበጋ ሐሩር ለኑሮ በማያመች ቤት ውስጥ ሰውን አፍኖ ማኖር በሃያ  አንደኛው መቶ  ክፍለ ዘመን ያለ ማሕበረሰብ ፍትሃዊነት ወይም ሰብዓዊነት ይለዋል ብሎ  ማሰብ ያዳግታል። ቅጣት ነው ካልተባለ  በስተቀር ። ስለሆነም የሚመሌከተው ሁሉ ትኩረት እንደሚስጥበት ተስፋ  እናደርጋለን።

·       በመጨረሻም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የጥቁር ሕዝብ ሁሉ መመኪያ  የሆነውን ይኸንን ታሪካዊ ቅርስ መጠበቅ  የገዳሙ ማህበረ መነኮሳት ሃላፊነት ብቻ አለመሆኑን ሊረዱት ይገባል። ገዳሙና  መነኮሳቱ የረጅም ጊዜ መከራን ጉስቁልና  አሳልፈዋል።

የዴር ሱልጣን ገዳም ለኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ክርስትና  ከቅኝ ግዛት በኋላ ወደ አፍሪካ የገባ ሳይሆን መሰረቱ እንደሆነና በኢየሩሳሌም ያለንን ድርሻ በአግባቡ መብት ተጠብቆ እንደሌሎች አገሮች ገዳሞች ሁሉ ተሟልቶ ለማንኛውም ጎብኚ ሲታይ አሁን የሚገኝበት አሳዛኝ ገጽ እንዲቀየርና ፡መነኮሳቱ ሰብዓዊ ክብር ተገፈው የሚኖርበትንና፥ በተለይ በትንሣኤ በዓል በየዓመቱ ከኮፕቶች ጋር ያለው ግብግብ እንዲቆም፡ ሲሉ ዛሬ በገዳሙ ውስጥ ስለገዳማቸው ክብር በጉስቁልና  እየኖሩ፡ እየተደበደቡና እንደ ሌላ  ፍጡር እየታዩ ግን በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ እያለፉ ዳዊት እየደገሙ ለዚህ ትውልድ ባደረሱ አባቶችና  እናቶች ስም ሁሉም ተገቢውን ስራ እንዲያከናውንና ኃላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን ልንጠይቅ እንወዳለን። ይህ ጊዜ አዲስ ምዕራፍ የምንጀምርበት ነው። ስለሆነም ከምንግዜውም በላይ የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መነሳት አለብን። የገዳሙን ታሪክ በሚገባ አጥንቶ ለሌላው ማሳወቅም ይሁን ሕጋዊ ወይም ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ መፈለግ ለቀጣይ ትውልድ የምናስቀምጠው ስራ አይደለም። በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሁሉ የገዳሙ ታሪክ በማጥናትም ሆነ የሕግ፡ የገንዘብና  የሌላ  ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ጥሪያችንን እናቀርባለን።” የጥቅሱ ጽሁፍ መጨረሻ

የዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳማት አሳዛኝ ገጽታዎችና ከዋናው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀበለበት፡ ተቀብሮ ከተነሳባት ዋናው ጎልጎታ ጋር ተያይዞ ያለ ታላቅ ክቡር ገዳም ነው 

 

 

 

 

 

 

 

 

እንዴት እንርዳ? የኛ ድርሻ ምን ይሁን?

ከላይ የተመለከተውን ጽሁፍ በማንበብና በየጊዜው በቅድስት ዓገር ለመሳለም እድል ገጥሞት ትንሣኤን በዓል ለማክበር ሄዶ የኢትዮጵያ ገዳማት የሚገኙበትን ይዞታና የመለኮሳቱን አኗኗር ያየና የሌሎቹን ደግሞ የካቶሊኮቹን ፣ የግሪክ፣ የራሽያ የሆኑ ገዳማት መቀደሶች፡የንዋየ ቅዱሳት መሸጫዎቻቸውን፣ የእንግዳ ማረፊያዎችን፣ ለተሳላሚዎች ማረፊያና የጉብኝት ዝግጅት ፣ የትምህርት፡የመሳሰሉትን ለተመለከተ በጣም ልብን የሚሰብር ነው። እንኩዋንስ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኝ ቀርቶ አምላክ ፈቅዶላቸው በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ለመሳለም የሄዱ እንኩዋን ከላይ በጽሁፉ ላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ተረድተው ይመለሳሉ የሚል ዕምነት የለንም። ቢያውቁና በሁኔታው ቢያዝኑም ምን ለማድረግ እንደሚቻልና ለመርዳት የሚያስችል መንገድ ስላላገኙ እንጂ ሁኔታውን በማስረዳት የስራ መርህ ከቀረበ ሁሉም ባለው ችሎታና ዓቅም እንደሚሳተፍ ዕምነታችን ፍጹም ነው።

በቅድስት ኢየሩሳሌም ለመሳለም አምላክ ፈቅዶልን በተገኘንበት ወቅት ሁኔታውን ለማየት ዕድል ስለፈቀደልንና ከላይ ያቀረብነውን በገዳሙ የተዘጋጀውን ጽሁፍ በማንበብ እንዴት አርገን ሁኔታውን ለማሳወቅና መላው ህዝብ ሊሳተፍ የሚልበትን በየጊዜው ስናስብ አሁን ያለውን ቴክኖሎጂ መጠቀም 40 ሚሊዮን ይገመታል ተብሎ የሚገመቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ካላቸው የዕምነት ጽኑነት አንጻር ፣ ሊያውቁበትና ሊሳተፉ የሚችሉበት መድረክ ካገኙ ይረባረቡበታል ብለን በማመን ሰለቤተክርስቲያናችን አንድነትና እድገት በአንድ እንድንነሳ እንዲረዳ  መነኩሴ ብለን የሰየምነውን /www.menekuse.org/  ድህ ገጽ ድርሻ ይዞ በመላው ዓለም ያሉ የኦርቶዶክስ ምእመናን እንዲያውቁትና የበኩላቸውን ከጥንት ጀምሮ የነበሩ አባቶች ያቆዩንን እንዳይጠፋ እንዲሳተፉና እንዲንከባከቡት፡ ዕድል ገጥሟቸው ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ለመሳለም የሚመጡ ምእመናን ደግሞ እመሰራረት ታሪኩን ፡ ዛሬ ያለበትን ሁኔታና ችግሩን በማየት ተሳትፏቸውን በማሳደግ እንድንገነባ የምንችልበትን መድረክ ለመፍጠር በበራሳችን ገንዘብና ባለን ዕውቀት ድርሻችንን ለማበርከት በተነሳሳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን የተዘጋጀ ነው።  

ይህም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ጽህፈት ቤት ላቀረበው ጥሪ ምላሽ ጅማሮ ስለሆነ ሁሉም የሃይማኖት አባቶች፡ ሰባኪያን መምህራን፣ የተለያይ ሙያ ያላችሁ ምዕመናን ፣ ይበልጥ ለማሳወቅና መብታችንን ለማስከበር ለምንጀምረው ጉዞ ሊረዳ የሚችለውን ያላችሁን ዶኪመንት ቪድዮ፡ የስራ ሃሳቦችና ፐሮጀክቶች በመነኩሴ ድህረ ገጽ በመሳተፍ ላላወቁ  እንዲያውቁ አዳብሩት እንዲሆም  ተሳተፉ እንላለን።

ለመነሻ ውይይትና ተግባር ይጠቅማሉ ብለን ውይይት እንዲደረግባቸውና ብሎም ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ በመነኩሴ የቀረቡ ሃሳቦችን በመመልከት ሃሳቡን ማዳበር፣ጥቂቶቹ ቀርበዋል።

 

የዴር ሡልጣን ገዳምን ለማስከበር

·       የዴር ሡልጣን ገዳም በግፍ የተነጠቅነውን መብታችን ለማስመለስ በመጀመሪያ ድጋፍ ዶኪመንቶችን ማሰባሰብ

·       ምን ያህል የገንዘብ፡የህግ፡ የአዋቂ ባለሙያ ተሳትፎ፡ የዲፕሎማሲና ግንኝነቶች እንደሚፈልግ ማጥናት

·       አስፈላጊ የሆነውን ገንዘብና መሰል ዝግጅቶችን ማደራጀት

·       ልዩ ብቃት ያላቸው ኢንተርናሽናል የህግ ባለሙያዎችንና ማፈላለግና መቅጠር

·       ለእስራኤል ፓርላማ ጉዳያችንን የሚያስረዱ ብቃት ያላቸው ታዋቂ ሎቢስቶች መቅጠር

·       የዓለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በመገናኘት የሚደርሰውን ግፍ ማሳወቅ

·       የዓለም ዓብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያን ጥንታዊነት ስለሚያውቁ ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ እንዲተባበሩ

·       የህግ ሙያ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ

·       የዴር ሱልጣን አከራካሪ የሆነውና  ልንነጠቅ ያለው ደባ የመብቱ ጉዳይ ከተፈታ ሌላው ስራ ቀላል ይሆናል።

 

ከላይ የተዘረዘሩት ከፍተኛ መደራጀትንና የገንዘብ ዓቅም ከሌለ እንኩዋንስ መጨረስ ለመጀመርም ከባድ ይሆናል። ነገር ግን ሃምሳ ሎሚ ላንድ ሰው ሸክም ነው ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ እንደሆነ ሁሉ መነኩሴ የምታምንበት 40 ሚሊዮን ምዕመን ከተባበረ ይህ በጣም ቀላል ይሆናል። ሃሳቡ ለውይይት ቀርቧል፡

6ቱን  በኢትዮጵያ መነኮሳት ቁጥጥር ያሉንን ገዳማትና ንብረት ለማጠናከር

·       እያንዳንዱን ገዳማት ምን እንደሚፈልግ ለማወቅና ብሎም ለማሰራት የእንጂነሪንግና የአርቴክት ሙያ ያላቸው ሰርቬይ የማድረግ ፕሮጀክት

·       ገዳሞቹ እስከዛሪ ተጠብቀው የቆዩት በጣም በጸኑ ከ60 በማይበልጡ መነኮሳት በመሆኑ የእነሱ ይዘታ የሚጠናከርበትን ፕሮጀክቶች አጥንቶ እንዲቀርብ

·       ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም መነኮሳት የሚጓጓዙበትና  ተሳላሚዎችን ለማገልገል የሚችል የትራንስፖርት አገልግሎት ጥናትና ስራ ዝርዝር በማቅረብ በርካታ ምዕመናን በግል ወይም በህብረት መሳተፍያ ማዘጋጀት፣

·       ለመሳለም የሚመጡ ምዕመናን ባሉን ንብረት ቦታዎች የማረፊያ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ ዝግጅት

·       ገዳሙ ከመላው ዓለም የሚመጡ ጎብኝዎች ስላሉት ልዩ የቤተክርስቲያናችንን ትምህርት ሊሰጥ የሚችልበት ጥናትና የተግባር ዝግጅት እንደሌሎች እንዲኖረን ማጥናትና መተግበር

·       ገዳሙ የንዋየ ቅድሳት ፡የጸሎት መጽሃፎችን እንደመሰል ቤተክርስቲያኖች ተሟልቶ ለምእመን እንዲቀርብ

·       ወደቅድስት አገር ምእመናን ለመሳለም የሚችሉበትን ማመቻቸትና 

·       በራሳቸው ለመሳለም የሚመጡ ከገዳሙ ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩበትን በማዳበር

  

ዳሙ ከተለያየ ዓለም የሚመጡ ተሳላሚዎች የሚጎበኝት ታላቅ መንፈሳዊ ቦታ እንደመሆኑ መነኮሳቱን ለበለጠ መንፈሳዊ አገልግሎት ማዘጋጀት የመሳሰሉትን ፕሮጀችቶች መጀመር ኢትዮጵያ ላሉንም ገዳማት ታላቅ ድጋፍና አርዓያ ይሆናል።

Ethiopian monastery in Jerusalem also known by the name Debre Sultan and also Dei res-Sultan, is actually on the roof of the church of the holy Sepulcher in Jerusalem is the last stronghold of the Ethiopian in Jerusalem. The Ethiopian Community has been residing in Jerusalem for the last two millennia, dating back to 4th century A.D. Till the 16th century Ethiopian in Jerusalem owned four Chapels in the church of the holy Sepulcher. These were chapel of our lady and of St. John the Evangelist, Chapel of St. Michael, Chapel of St. john the Baptist and chapel of St. Mary Magdalene. However, they lost all these chapels due to the luck of aid from the Ethiopian Emperor. From the written documents of French pilgrim Charles Philippe de Champermony we come to know about the Ethiopian presence in Debre they still preserved the Ethiopian Monastery in Jerusalem by sacrificing their lives and health. I the 18th Century an Egyptian named Ibrahim Guihari and his 8 slaves came to the Monastery and claimed the monastery. Therefore, the Copts intervened and forces the priest of Ethiopian monastery in Jerusalem to hand over the key to them. The worst enemy struck the Ethiopian monastery of Jerusalem in 1838 in the form of a plague which killed all the nuns and monks save two. There for the Copts and the Armenians burnt down the library of the monastery and all the valuable and manuscripts were lost.

In 1850 however again the Ethiopian got the key to monastery through the Copts kept the chapels of St. Michael and the chapel of the four Creatures permanently locked for 80 years from the year 1862. Therefore the Ethiopian were forced to erect a huge tent for celebrating various festivals and this tradition is still followed. globerx24

 

When you enter the Ethiopian monastery in Jerusalem, then you will find that the whole church is carpeted. The walls and columns of the monastery have painting depicting the holy Family and the famous saints of Ethiopia. But the look of the church might disappoint you since it shows the poverty of in which the community is submerged.

Leave a comment

Comments

  • No comments found