የመነኩሴ ድህረ ገጽ ዓላማ
የመነኩሴ ድህረ ገጽ / ዓላማ
የቤተ ክህነት መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 40 ሚሊዮን ምዕመናን ፡ 400 ሺህ ካህናትና 1000 ገዳማት እንዳሏት ያመለክታል።
ይህ ከፍተኛ የዕምነቱ ተከታይ ከዳር ሳይቆም በአንድነት ከተሳተፈ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ቤተክርስቲያናችን፟:-
1. በየጊዜው በተከሰቱ ተጽእኖዎች የተፈጠረውን መለያየት በጋራ በመወያየት አንድነትን ለማስፈን፣
2. በቅድስት ሃገር ኢየሩሳየሌም ያሉንን ገዳማት መብት ለማስከበርና ለማጠናከር፣
3. የማፍረስ፡የመዝጋትና መቃጠል፡ ክርስቲያኖችን ማፈናቀል እንዲቆሞ ሰላምን ለማምጣት
4. ካህናትና ምዕመናን በቤተክርስቲያን አከፋፈት ዝብርቅርቅ ቆም ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን
5. ስብከት፣መዝሙራት ፡ንዋየ ቅድሳት፡ ስዕሎችን በማስተማር የልዩ ነት ንትርኮች ለማስወገድ
6. ከቄስ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ጠንካራ የትምህርት ማዕከል እንዲኖረን በአንድነት ለመስራት፣
7. በየጊዜው ከመለመን ቋሚ ደራሽ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የእርዳታ ድርጅት ማቋቋም
8. ዜማ ፡ቅኔ፡ ማህሌት፡ ቅዳሴ ፡መጻህፍት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዳብረው ለትውልለማሳለፍ ፣
9. በየቦታው ያልተሟሉ ትንንሽ ቤተክርስቲያን መክፈት ሳይሆን በትልቅ ራዕይ እንዲሰሩ ማስተማር
10. አማኞችን ከጎጂ ልማዶች ለማላቀቅ የሚያስችሉ የዳግም ትንሳኤ መንፈሳዊ ማዕከል መዘርጋት፣
11. በንብረትና ጥቅም በየቤተክርስቲያኖች የተዛመተው የክስና ጠብ ወረርሽኝ ለማስወገድ፡
ይይት መድረክና የተግባር መነሻ እንዲሆን ከልብ በመነጨ ክርስቲያናዊ ፍላጎት ምእመናን እንዲሳተፉና ለቤተክርስቲያናችን ጥንካሬ በማሰብ የቀረበ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ጥሪና ጅምር ድህረ ገጽ ነው።
ዓላማውም ቤተክርስቲያናችን ሳትከፋፈል የነበራት አንድነት ተመልሶ እንደጥንቱ በአንድነት በፍቅርና በሰላም እምላክን የምናመሰግንበት ፣ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ለመወረስ የምንችልበት እንድትሆን ይህንን የመነኩሴ ድህረ ገጽ www.menekuse.org በመጀመር ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትተከታይ በየዓምዱ በቀረቡት ሃሳቦችና ሌሎችንም በመጨመር ባለው የሙያ ችሎታና አቅም በመሳተፍ ለቤተክርስቲያናችን ህልውና ለተግባር ለማሳደግ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ በማመን ጀምረናል።
ይህንንም የፍቅር አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ የአማላጅ እናቱ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም፡ ልመና ፡የተራዳኢ መላእክትና የጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት ለቤተክርስቲያናችን ዘላለማዊ እንድነት እንድናመጣ ይርዳን። አሜን!!!!!!!!!!!
If you are a professional please join us to help something in some way.
If you are a professional please join us to help something in some way.
God Bless You All.
Melekuse Team
Info@melekuse.org