የመነኩሴ ድህረ ገጽ ዓላማ

 

የመነ ድህረ ገጽ / ዓላማ

www.menekuse.org

      የቤተ ክህነት መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ጊዜ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 40 ሚሊዮን ምዕመናን ፡ 400 ሺህ ካህናትና 1000 ገዳማት እንዳሏት ያመለክታል።

       ይህ ከፍተኛ የዕምነቱ ተከታይ ከዳር ሳይቆም በአንድነት ከተሳተፈ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ቤተክርስቲያናችን፟:-

                     1.        በየጊዜው በተከሰቱ ተጽእኖዎች  የተፈጠረውን መለያየት በጋራ በመወያየት አንድነትን ለማስፈን፣

 

2.        በቅድስት ሃገር ኢየሩሳየሌም ያሉንን ገዳማት መብት ለማስከበርና ለማጠናከር፣

 

3.        የማፍረስ፡የመዝጋትና መቃጠል፡ ክርስቲያኖችን ማፈናቀል እንዲቆሞ ሰላምን ለማምጣት

 

4.        ካህናትና ዕመናን በቤተክርስቲያን አከፋፈት ዝብርቅርቅ ቆም ስርዓቱን የተከተለ እንዲሆን

 

5.        ስብከት፣መዝሙራት ንዋየ ቅድሳት፡ ስዕሎችን በማስተማር የልዩ ነት ንትርኮች ለማስወገድ

 

6.        ከቄስ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ጠንካራ የትምህርት ማዕከል እንዲኖረን በአንድነት ለመስራት፣

 

7.        በየጊዜው ከመለመን ቋሚ ደራሽ ዓለ አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የእርዳታ ድርጅት ማቋቋም

 

8.        ዜማ ፡ቅኔ፡ ማህሌት፡ ቅዳሴ ፡መጻህፍት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዳብረው ለትውልለማሳለፍ    

 

9.        በየቦታው ያልተሟሉ ትንንሽ ቤተክርስቲያን መክፈት ሳይሆን በትልቅ ራዕይ እንዲሰሩ ማስተማር

 

10.     አማኞችን ከጎጂ ልማዶች ለማላቀቅ የሚያስችሉ የዳግም ትንሳኤ መንፈሳዊ ማዕከል መዘርጋት፣

11.   በንብረትና ጥቅም በየቤተክርስቲያኖች የተዛመተው የክስና ጠብ ወረርሽኝ ለማስወገድ፡

ይይት መድረክና የተግባር መነሻ  እንዲሆን ከልብ በመነጨ  ክርስቲያናዊ  ፍላጎት ምእመናን እንዲሳተፉና ለቤተክርስቲያናችን ጥንካሬ በማሰብ የቀረበ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን  ጥሪና  ጅምር ድህረ ገጽ  ነው።

 

ዓላማውም ቤተክርስቲያናችን ሳትከፋፈል የነበራት አንድነት ተመልሶ እንደጥንቱ በአንድነት በፍቅርና በሰላም እምላክን የምናመሰግንበት ፣ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን ለመወረስ የምንችልበት እንድትሆን ይህንን የመነኩሴ ድህረ ገጽ www.menekuse.org  በመጀመር ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትተከታይ በየዓምዱ በቀረቡት ሃሳቦችና ሌሎችንም በመጨመር  ባለው የሙያ ችሎታና አቅም በመሳተፍ ለቤተክርስቲያናችን ህልውና  ለተግባር ለማሳደግ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ በማመን ጀምረናል።

          ይህንንም የፍቅር አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ የአማላጅ እናቱ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም፡ ልመና ፡የተራዳኢ መላእክትና የጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት ለቤተክርስቲያናችን ዘላለማዊ እንድነት እንድናመጣ ይርዳን። አሜን!!!!!!!!!!!

 

 

 

 

 

 

 

                                                                                                                                                                                                                  

 

          

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

If you are a professional please join us to help something in some way.

 

 

ለምን የድህረ ገጹ/ዌብሳይቱ/ ስም መነኩሴ ተባለ?

ክርስትና እንዳይስፋፋ ለ300 ዓመታት ያህል ንጉስ ቁስጠንጢኖስ ክርስትና ህጋዊ ሃይማኖት እንዲሆንና ክርስቲያኖችም በነጻነት እንዲያመልኩ እስካወጅበት ድረስ ክርስቲያኖች ሁሉ ህይወታቸውን ለክርስቶስ ፍቅር በመሰዋት የሰማእትነትን ከብር ተቀዳጅተው ነበር። ከዚያ በሁዋላ ግን ለሃይማኖት በመሞት የሚገኘው ሰማዕትነት ሲያበቃ ክርስቲያኖች የጌታችን ኢየሱስን ፈለግ ለመከተል ሰማእት ለመሆን በፈቃደኝነት እራሳቸውን በማደህየት ፡ የዚህ ዓለምን ገንዘብና ምቾት ሳይሆን መላ ሕይወታቸውን ለሞተላቸው የፍቀር ለአምላክ ሰጥተው ለእምነታቸው ጽናት ለቤተክርስቲያናችው ዕድገትና ጥንካሬ መኖር በመምረጥ በተናጠል በበረሃ ተለይተው በጾምና በጸሎት በመንፈሳዊ ህይወት የሚኖሩት መጠሪያ  መነኩሴ” ይባላሉ። እንዱሁ ክርስቲያን የሆንን ሁሉ በገንዘብና ጥቀም ሳንሸነፍ ለክርስትና ህይወታችን መስዋዕትነትና  ክርስቲያናዊ ህይወትን እንድንኖር የነሱን አርዓያ ለመከተል መጣርን  በማመልከት የመነኩሴ ጾምና በጸሎት ከአምላክ አስታራቂ እንደሚሆን ለኛም የመነኩሴ ጸሎትና ልመና አስታራቂ መንፈስን እንድንዲልክልንና በእንድ እንድንነሳሳ መነኩሴ ተብሎ  ተሰይሟል።

 

 

በእንግሊዝኛ አገላለጹ _MENEKUSE/monk or nun is an individual who is totally dedicated his or her lives to GOD, taken the vows of poverty, chastity and obedience, serve the church in special way, work for salvation of the world, and strive for the perfection of charity in His/Her own lives. MENEKUSE is an outstanding sign of the Church and a witness of Jesus Christ

 

 

 

የድህረ ገጹ መጀመሪያ ፎቶግራፍ ምንድነው???

 

 

በድህረገጹ ያለው ፎቶግራፍ  በእርግጥ ምንድነው የሚያሰኝ ነው። ማወቁ ደግሞ መንፈስን የሚፈውስ የክርስትና አውታራችን ነው። ፎቶግራፉ ከላይ የተነሳና ከመላው ዓለም የተሰበሰቡ ክርስቲያኖች ዙሪያውን ከበው ለመዳሰስ የሚታገሉበት በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ጎልጎታ ውስጥ የሚገኘው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከሲኦል ለማውጣት ተወግሮ ተሰቅሎ ተቀብሮ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት የመቃብሩ ቦታ ነው ። ከፓትርያርክ እስከ ተራ ምዕመን ያለነው የክርስቶስ ተከታይ ስለሆንን የጌታችንን ኢየሱስ ፍቅር ሰላም እያሰብን ቂምን ትተን ፍቅርን፡ ጠብን ትተን ሰላምን ለማምጣት ለእምነታችን እንድንቆም ድህረገጹን በከፈትን ቁጥር ለፍቅሩ እንድንገዛ ለማሳሰብ ነው።

የድህረ ገጹ አዘጋጆች እነማን ናቸው? በቤተክርስቲያናችን ከምንሰማውና በግል ንባብ ካገኝነው ዕውቀት ሌላ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ትምህርት የሌለን ተራ ምዕመናን ስንሆን በቤተክርስቲያናችን ላይ የምናየው ሁኔታን ስላሳዘነን ያቅማችንን ለማበርከት የተነሳን ተራ ምዕመናን ነን።  

If you are a professional please join us to help something in some way.

 

God Bless You All.

Melekuse TeamM

Info@melekuse.org

 

የድህረ ገጹ አዘጋጆች እነማን ናቸው?

በቤተክርስቲያናችን ከምንሰማውና በግል ንባብ ካገኝነው ዕውቀት ሌላ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ትምህርት የሌለን ተራ ምዕመናን ስንሆን በቤተክርስቲያናችን ላይ የምናየው ሁኔታን ስላሳዘነን ያቅማችንን ለማበርከት የተነሳን ተራ ምዕመናን ነን።   

continue.

,
CONTINUE READING