የፋና እሳቤ

=================================================================

የፋና እሳቤ

በቅዱስ ማቲዎስ  ምዕራፍ 5 ክቁ 13 -16 ጊታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ እናንት ጨው ናችሁ። ውሃውን ዓለም አጣፍጡ ፣ የዓለም  ብርሃናችሁ የጨለመን ሁሉ አብሩ፣ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልተሰወር አይቻላትም ። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።” እንዳለን የተረጂና ተረጂ ሳይሆን ሁሉም በተሰጠው ጸጋ በአንድ ጨለማ ክፍል ፣ አንድ  የመብራት አምፖልና አምፖሉን በሚያበራ ሰው ትብብር ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ   ምዕመናንና ቤተክርስቲያን ተጣምረው ፋና እንዲሆኑ የሚያስችል ኦርቶዶክሳዊ  የበጎ ተግባር እሳቤ ነው። 

ፋና ለምን? እንዴት 
⦁     ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር  89/90 ቁ 10” የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ፡ ዓመት ፡ ቢበረታም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው። ከእኛ ቶሎ ያልፋልና” ሁላችንም ሰባና ስማኛአ ስንደርስ የነበረን እውቀት ባዲስ ተተክቶ እርዳታ ፈላጊ እንሆናለን 
⦁     በጥበብና ሃብት የከበረው ንጉስ ሰሎሞን በመጽሃፈ መክብብ ምዕራፍ 3 ቁጥር 12 “ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ” ባለን ጊዜ እኛው ለበጎ ካላዋልነው የሰሰትለትን ሁሉ  ማን እንደሚወስደው ሳናውቅ ጥለነው እንሄዳለን።
ና እንዴት? በምን?  

ፋና ድርጅት በማቋቋም ገንዘብ ሰብስቦ የሚሰራ አይደለም፣ ፋና በጽኑ እምነት በግል አነሳሽነት በዓቅም የተዳከመ ቤተ ክርስቲያንንና የምዕመናን ህይወት ቀያሪ ስራ  በመስራት አርዓያ መሆን ነው። ይህንንም በሌላ ቦታ ሞክረን ጥሩ ውጤት አስገኝቷል። ካለን ጸጋ  ጋት የሚያክል በመቆንጠር ብዙ መስራት ስለሚቻል ፋና በኢትዮጋት ተብሏል።   ጋት ማለት ከአባቶች መለኪያ  ትልቁ  ክንድ ፣ ከዚያም ስንዝር፣ አነስተኛው ጋት ነው።  (ጋት ማለት  የአራት ጣቶች  ስፋት ያህል ) የበረታ ክንድ ፣ ስንዝር ሁሉም   ጋት  እንዲሰጥ የሚጣራ ኦሮቶዶክሳዊ  የተግባር ተሳትፎ ማለት ነው። 

ፋና በኢትዮጋት የገንዘብ  ምንጮች  

ከብክነት ጥቂት ልገሳንና  ያሉንን ትርፍ ነገሮችን አስቦ ለሌላቸው መስጠት  ከደስታ ዝግጅቶች፣    ልጅ ሲወለድ  ፣ ከክርስትና ፣ ከልደት፣  ከምርቃት ፣ ከሰርግ ፣ ሹመት ፣ ዝክር ድግሶች ትንሽ መታስቢያ፣ በጎ ስራ አስቦ መቆንጠር ነው    

3  ከሃዘን ወቅት ዝግጅቶ፣   ሃዘንን በለቅሶ በተዝካርና ትልቅ ሃውልት ብቻ በመገንባት ሳይወሰን  አስፈላጊውን  ዝግጅት በመጠኑ  አድርጎ ለሟች ዘለዓለማዊ ማስታወሻ የሚሆን  ቋሚ  ለመታሰቢያ መስራት ልምድ ማዳበር ነው።

 

አንድ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት “እኛ መነነኮሳት በገዳም ብንኖርም ስራችን ለዓለም ለመፀለይ ነው ። እዚህ ገዳም ተቀምጠን ከዓለም የማንወጣ እንዳለን ሁሉ ከተማ ተቀምጠው የመነኩሴ ተግባር በሚያከናውኑ የጸኑ ክርስቲያኖች አገልግሎት ስለሆነ ገዳማትና ቤተክርስቲያን የሚጠበቁት በዓለም ውስጥ ሆነው በፍቅር ሰርተውና በእምነት ጸንተው ቤተክርስቲያንን የሚያጠ ናክሩ አገልጋይ ምዕመናኖች ሁሉ መነኩሴ ናችው” ብለዋል።  ሁላችንም በዚህ በፋና ጉዞ ከተሳተፍን ሁላችንም መነኩሴዎች ነን።

 

 

በፋና የእርዳታ ተግባራት 


1.  
ቤተ ክርስቲያናትን ማጠናከር 

የኢኦትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ፈተና ቢያጋጥማትም እስከ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ማብቂያ 1966 ድረስ የነበሩት ነገስታት ለቤተክርስቲያን ታላቅ አክብሮት ስለነበራቸው የጠፉት እየተገነቡ በጥሩ ቀጥላለች 1966  ስልጣን የያዘው የደርግ መንግስት ሃይማኖት ጠል ፖሊሲ ስለሚከተል  ያለአግባብ  ህብትዋን  ወርሶ ፓትርያርክዋን ገድሎ አስተዳደርዋ እንዲዳከም የጀመረው መቅሰፍት እስከ አሁንም እየተባባሰ ቀጥሎ ህልውናዋን እየፈተናት ቢሆንም ዛሬ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን 50 ሚሊዮን የሚገመቱ አማንያን በርካታ የሃይማኖት አባቶች  ስባኪ መምህራን በተለያየ  ዘመናዊው የምዕራባውያን ትምህርት እስከ ዶክትሬትና ፍልስፍና ቢሰለጥኑም በሃይማኖታዊ ትምህርትም እስከ ዶክትሬት  በመማር ሃይማኖትን የሚታደጉ፣  በአንገታቸው ማህተባቸውን እስከ ሞት አስረው ጸንተው  የሚቆሙ   አጽዋማትን አምነው የሚጾሙ  ስርዓተ ቅዳሴን ማህሌቱን ዝማሬውን  የሚያንቆረቁሩ ለጉባኤና ለታቦት ንግስ አገር አቋርጠው የሚጓዙ   ሃይማኖት የሚሰራጩባቸው ሬዲዮና ቴሊቪዥኖች የተደራጉ ማህበሮች   የሰንበት ትምህርት ቤቶች በገንዘብና በስልጣንም ከፍተኛ ቦታ ያላቸው አማኞች ያሉበት  ዘመን ከመሆኑም ባሻገር  በደረሰባቸው በደል ኦርቶዶክሳውያን በመላው ዓለም በመበተናቸው  ባሉበት ሁሉ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን  በዓለም ከተሞች  እያበበች የሌሎች ሃገሮች  ዜጋዎችም  እምነቱን  እየተቀበሉ  ጋብቻቸውን በቅዱስ ቁርባን የሚፈጽሙባት ሆናለች

ሌሎች ለሚያምኑበት እምነት በማያውቁት ሃገርና ህዝብ ተጉዘው ገበተው  ቤተክርስቲያናቸውን ገንብተው   የሌሎች እምነት ተከታዮች ሳይቀሩ በጥሩ ምግባር ጥሩ ትምህርት ይሰጣሉ ብለው ልጆቻቸውን የሚልኩባቸው ከመዋዕለ ህጻናት እስክ ዩኒቨርስቲ የተሟሉ ትምህርት ቤቶች የጤና አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና  ክሊኒክና ሆስፒታሎች ደካማ አቅም ላላቸው መደጎሚያ አገልግሎቶችና የነጻ የሙያና የትምህርት ዕድሎች  መፍጠር እንደቻሉ ሁሉ ኦርቶዶክሳውያንም ለኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ተግባር /ORTHODOX TEWAHEDO MISSIONARY SERVICE/  ባለን ትልቅ አቅም  በርካታ ስራዎች ስራዎች የቤተክርስቲያናትን ህልውና መጠበቅና  ማስቀጠል በመሆኑ  

  •  ነባር  የፈራረሱ ቤተክርስቲያናትን   እንዳይዘጉና እርዳታ እንዲጠናከሩ ማድረግ
  • ለእምነት ለአገልግሎትና ለካህናት የሚያስፈልግ ወጭ ለመሸፈን ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲኖር ማገዝ፣
  • የምዕመናን ተዳከመው እንዳይጠፉና እንዲጠነክሩ   ኑሮ  የማሻሻያ ዕድሎች እንዲፈጠሩ  ካለን እውቅት በማካፈል  ማሳደግ፣  
  • ቤተ ክርስቲያን  እንደግል ቤታችን በንጽህና ተጠብቃ እንደ ጥንቱ ባማሩ የዛፍ ተክሎችና  ፍራፍሪዎች ማሳመር 
  •  በንግስና በጠበል ጉዞ ወቅት ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናን  የሚለወጥ ስራዎችን  ይዞ የመስራት ልማድ  ማዳበር 
  • አዳዲሶች አማኞች እንዲመጡ ተጨማሪ አብያተ ክርስቲያናት  እንዲሰሩ ማድረግ

2 የቄስ ትምህርት ቤትን ማሳደግ  

ዘመናዊ ትምህርት ሲጀመር እንደማይጠቅሙ የተገፉት የቂስ ትምህርት ቤቶች በመቋረጣቸው ትውልዱ የኦርቶዶክስን አምልኮ ስርዓትና ስነምግባር  ክልጅነት ተቀርጽው የሚያዱጉበት ኧድልም ተዘግቶአል። ተተኪ ካልተዘጋጀ   አሁን ያሉት ታላላቅ ቤተክርስቲያናትም በምዕራቡ ዓለም ተተኪ በማጣት  ወደ ቡና ቤትነትና ንግድ ድርጅት እንዳይቀየሩ ኦርቶዶክሳዊት ቢተክርስቲያናችንም  በኦርቶዶክስ ስነምግባር  ታንጸው ከዘመናዊ ትምህርት ጋር  ተጣምሮ እንዲማሩ መሰረት ለመጣል የመጀመሪያው እርምጃችን  የቄስ ትምህርት ቤቶች እንደገና በየቤተክርስቲያን እእንዲያብቡና  ቀስ በቀስ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም  ደርሰው ለኦርቶዶክስ ዘብ የሚቆም ትውልድ  ለማፍራት       
    ቤተክርስቲያናት ሁሉ  የቄስ ትምህርት ቤት  እንዲኖር  የመማሪያ ክፍል እንዲኖር   ለአስተማሪ  ደሞዝ   ለትምህርት መሳሪያዎች ድጋፍና   ማደራጀት
     ከቂስ ትምህርት ቤት  ከሚያጠኗቸው ኦርቶዶክሳዊ  ጥናት ጋር የግዕዝን ትምህርት አብረው እንዲማሩና ቤተክርስቲያንዋን ስርዓት እንደልብ የሚከታተሉና በግዕዝ የተጥሽጻፉ መጻህፍትን  አንብበው በመረዳት ለሃገርም ጭምር  እንዲጠቅሙ  ወደ ዘመናዊ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲገቡም ሳይቋረጥ ድጋፍ እየተደረግላቸው  የጀመሩትን ትምህርት እንዳይረሱ ተከታታይ ትምህርት የሚያገኝበትን ማመቻቸት እጅግ ወሳኝ ይሆናል።

 ወጣቶች በተለያዩ ልማዶች ነጻ ሆነው ታላቅ የቤተ ሰብ ኃላፊ እንዲሆኑ ቀስ በቀስ  ኦርቶዶክሳዊ  አስተሳሰብና ምግባር በስርዓተ ትምህርቱ ሊካተቱ የሚችሉበት  የራሳችን የሆኑ የአንደኛ ሁለተኛ ደረጃና በሂደት እስከ ክፍተኛ ዩኒቨርስቲዎች ለማቋቋም  እስክንችል ወጣቶች ለቤተሰብና ለሃገር የመታዘዝ ታማኝ ዜጋ እንዲሆኑ  በእቅድ   ይዞ ማሳፋፋት ያስፈልጋል።  

የኔ ቢጤን /የጽድቅ በር

በቅዱስ ሉቃስ ወንጊል ምዕራፍ 16 ክቁ 19 - 31  የተጠቀሰው የሀብታሙ ሰውና አላዛር ምሳሌ ሁላችንንም አተኩረን ልንማረውና ልንተርጉመው የሚገባንን ታላቅ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አበክሮ እንድናደርገው የሚወደው ተግባር   በጣም አስበን መተርጎም ከቻልን ኦርቶዶክሳውያንን ወደ ትልቅ ደረጃ ያሻግረናል።  እኛ ጥሩ ለብሰን በሞቀ  በቤትክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠን አስቀድሰን በጥሩ የተዘጋጀ  መክፈልት ቀምሰን ቤታችንም ገብተን በጥሩ ቤት የመኖርና የመመገብ ህይወት  እያለን   ስንገባም ሆነ ስንመለስ  ብዙ ጊዜ እያለፍን አንዳንዴም  ትቂት ሳንቲም  ወይም ቁራሽ  ሰጥተን  አልፈናቸው የምንሄደውን  በተለምዶ " የኔ ብጤ" ብለን የምንጠራቸውን ምዕመናን ወገኖቻችን  ከተሰጠን ፋና የነሱንም ህይወት ደረጃ በደረጃ  ለመቀየር 

  • ከፀሃይ፣ ከዝናብና ብርድ ተገላግለው የሚቀመጡበት  ቦታ ከቤተክርስቲያኑ አጠገብ እንዲኖር ማገዝ   
  •  ለነሱ መለገስ ለጌታችን መለገስ ነውና ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄ አስበን ይዘን በመሄድ  የምንሰጣቸውን  ምጽዋት ስርዓት ባለው መልክ እንዲያገኙ ማድረግ 
  •  ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱት ለልመና በቻ ሳይሆን ቃለ እግዚአብሄርን እነሱም እንዲሰሙ  ማመቻቸት  
  •  ሕይወታቸው ሙሉ በልመና እንዳይሆን መስራት ለሚችሉ ባቅማቸው የስራ ዕድል መፍጠር   
  •  የተለያየ ሙያ እንዲማሩ ሙያዊና፣ የገንዘብ እገዝ አድርጎ ስራ እንዲሰሩ የሚያስችል  ልምድ በማዳበር ቤተ ክርስቲያናችንን በተጎሳቆሉ የኔብጤዎች የተከበበች  እንዳትሆን መስራት ይገባናል። 

4  ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ህጻናትና ልጆች እንከብካቤ

በየቤቱ ብዙ ወላጆች ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ልጆቻቸውን ይዘው መኖር ስለማይችሉ በመንገድ ላይ ይለቋቸውል።  ሰው ከልጁ በላይ የሚወደው ነገር የለም።   ጤነኛ ልጅ ማሳደግ  ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ልጅ ያለው ሰው ይረዳዋል። ለወላጆቹም ሆነ ለልጆቹ ከባድ መሆኑን እንዲሁም ይህን መካፈል በአምላክ ዘንድ ታላቅ ዋጋ ያስገኛልና  ትኩረት በመስጠት 


   ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ልጆች በፍቅር እንደ ልጆቻችን የማቅረብ ባህል ማዳበር
   የሚመጥናቸው ዝግጅት በየዕድሜያቸው ማሳተፊያ መንፈሳዊ ዝግጅት እያቀረቡ በክርስቲያን ፍቅር መቅረጽ
በየመንገዱ ከመለመን እንዲወጡ  ባሉበት በቤተሰባቸው እርዳታ ማድረግና  ባላቸው አቅም ሊሰሩ የሚችሉትን ስራ እንዲሰሩ ማገዝዝ

5 ተከራይ ባልቤትና ገበሬውን  የተሻለ ባለቤት የማድረግ 


ለሰው ልጅ ቤት መኖር ታላቅ የሕይወት ደስታ መሆኑን የራስ ቤት ያለው ለመጀመሪይ ባለቤት ሲሆን ያለው ደስታ እጅግ ትልቅ መሆኑን    ዕድል ያገኙ ያውቁታል። በከተማም ሆነ  በገጠር  አብዛኛው ወገኖቻችን የሚኖሩባቸው ቤቶች በጣም አሳዛኝና የሃገራችንን የመጨረሻ ድህነትና ጎስቋላ ህይወት ያመለክታሉ። ለረጅም ዓመታት ብዙ የውጭ ረጂዎች እርዳት እያሉ ቢመጡም ችግሩ ምንም አልተነካም። ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንዲሉ በዚህ መልክ  ይህን መቀየር የሚያስችሉ እቅዶችና  ይዞ  ለመርዳት ጥረት መጀመር  ታላቅ ለውጥ ያስገኛል 

 

 

 

 


  

5 ተከራይን ባልቤትና ገበሬውን  የተሻለ ባለቤት የማድረግ  ለሰው ልጅ ቤት መኖር ታላቅ የሕይወት ደስታ መሆኑን የራስ ቤት ያለው ለመጀመሪይ ባለቤት ሲሆን ያለው ደስታ እጅግ ትልቅ መሆኑን    ዕድል ያገኙ ያውቁታል። በከተማም ሆነ  በገጠር  አብዛኛው ወገኖቻችን የሚኖሩባቸው ቤቶች በጣም አሳዛኝና የሃገራችንን የመጨረሻ ድህነትና ጎስቋላ ህይወት ያመለክታሉ። ለረጅም ዓመታት ብዙ የውጭ ረጂዎች እርዳት እያሉ ቢመጡም ችግሩ ምንም አልተነካም። ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ እንዲሉ ፋና በኢትዮጋት እሳቤ በሕይወት እያለን ባለን ሙያና የተለያዩ  የድግስ ዝግጅቶቻችንና ብክነቶችን በመቆጣጠር  ስንዝር ቢያንስ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን  የአራት ጣቶችን ስፋት ያህል ጋት ብቻ  ብንቆነጥር ታሪክ መፍጠር እንችላለን።

 

 

 

Leave a comment

Comments

  • No comments found