ፋና

የፋና እሳቤ

በቅዱስ ማቲዎስ  ምዕራፍ 5 ክቁ 13 -16 ጊታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ እናንት ጨው ናችሁ። ውሃውን ዓለም አጣፍጡ ፣ የዓለም  ብርሃናችሁ የጨለመን ሁሉ አብሩ፣ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልተሰወር አይቻላትም ። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።” እንዳለን የተረጂና ተረጂ ሳይሆን ሁሉም በተሰጠው ጸጋ በአንድ ጨለማ ክፍል ፣ አንድ  የመብራት አምፖልና አምፖሉን በሚያበራ ሰው ትብብር ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ   ምዕመናንና ቤተክርስቲያን ተጣምረው ፋና እንዲሆኑ የሚያስችል ኦርቶዶክሳዊ  የበጎ ተግባር እሳቤ ነው። 

ፋና ለምን? እንዴት 
⦁     ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር  89/90 ቁ 10” የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ፡ ዓመት ፡ ቢበረታም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው። ከእኛ ቶሎ ያልፋልና” ሁላችንም ሰባና ስማኛአ ስንደርስ የነበረን እውቀት ባዲስ ተተክቶ እርዳታ ፈላጊ እንሆናለን 
⦁     በጥበብና ሃብት የከበረው ንጉስ ሰሎሞን በመጽሃፈ መክብብ ምዕራፍ 3 ቁጥር 12 “ሰው ደስ ከሚለውና በሕይወቱ ሳለ መልካምን ነገር ከሚያደርግ በቀር መልካም ነገር እንደሌለ አወቅሁ” ባለን ጊዜ እኛው ለበጎ ካላዋልነው የሰሰትለትን ሁሉ  ማን እንደሚወስደው ሳናውቅ ጥለነው እንሄዳለን።
ና እንዴት? በምን?  

ፋና ድርጅት በማቋቋም ገንዘብ ሰብስቦ የሚሰራ አይደለም፣ ፋና በጽኑ እምነት በግል አነሳሽነት በዓቅም የተዳከመ ቤተ ክርስቲያንንና የምዕመናን ህይወት ቀያሪ ስራ  በመስራት አርዓያ መሆን ነው። ይህንንም በሌላ ቦታ ሞክረን ጥሩ ውጤት አስገኝቷል። ካለን ጸጋ  ጋት የሚያክል በመቆንጠር ብዙ መስራት ስለሚቻል ፋና በኢትዮጋት ተብሏል።   ጋት ማለት ከአባቶች መለኪያ  ትልቁ  ክንድ ፣ ከዚያም ስንዝር፣ አነስተኛው ጋት ነው።  (ጋት ማለት  የአራት ጣቶች  ስፋት ያህል ) የበረታ ክንድ ፣ ስንዝር ሁሉም   ጋት  እንዲሰጥ የሚጣራ ኦሮቶዶክሳዊ  የተግባር ተሳትፎ ማለት ነው። 

ፋና በኢትዮጋት የገንዘብ  ምንጮች  

ከብክነት ጥቂት ልገሳንና  ያሉንን ትርፍ ነገሮችን አስቦ ለሌላቸው መስጠት  ከደስታ ዝግጅቶች፣    ልጅ ሲወለድ  ፣ ከክርስትና ፣ ከልደት፣  ከምርቃት ፣ ከሰርግ ፣ ሹመት ፣ ዝክር ድግሶች ትንሽ መታስቢያ፣ በጎ ስራ አስቦ መቆንጠር ነው    

3  ከሃዘን ወቅት ዝግጅቶ፣   ሃዘንን በለቅሶ በተዝካርና ትልቅ ሃውልት ብቻ በመገንባት ሳይወሰን  አስፈላጊውን  ዝግጅት በመጠኑ  አድርጎ ለሟች ዘለዓለማዊ ማስታወሻ የሚሆን  ቋሚ  ለመታሰቢያ መስራት ልምድ ማዳበር ነው።

 

አንድ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት “እኛ መነነኮሳት በገዳም ብንኖርም ስራችን ለዓለም ለመፀለይ ነው ። እዚህ ገዳም ተቀምጠን ከዓለም የማንወጣ እንዳለን ሁሉ ከተማ ተቀምጠው የመነኩሴ ተግባር በሚያከናውኑ የጸኑ ክርስቲያኖች አገልግሎት ስለሆነ ገዳማትና ቤተክርስቲያን የሚጠበቁት በዓለም ውስጥ ሆነው በፍቅር ሰርተውና በእምነት ጸንተው ቤተክርስቲያንን የሚያጠ ናክሩ አገልጋይ ምዕመናኖች ሁሉ መነኩሴ ናችው” ብለዋል።  ሁላችንም በዚህ በፋና ጉዞ ከተሳተፍን ሁላችንም መነኩሴዎች ነን።

 

የፋና ኢትዮጋት እሳቤ ክንውን ሂደት 

  1. የፋና እሳቤ የእረጂና ተረጂነት ሳይሆን አምፖልና አብሪ ተባብረው ብርሃን እንድሚፈጥሩ ፋና መሆን

  2. ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን ሌላ ቢያንስ አንድ ደካማ ቤተ ክርስቲያንና የቄስና የግዕዝ ትምህርት እንዲኖር መርዳት  

  3. ክንውኑ ሌሎችን እንዲያበረታ በመነኩሴ መሳተፊያ ዘዴዎች ለደጋፊዎች ማሳወቅ 

  4. መንፈሳዊ ስራ ህይወት እስካለ ቀጣይ ስለሆነ ሌሎችን ለመስራት ተባብሮ መቀጠል

 

ለመነኩሴ ድህረ ገጽ  የፋና ኢትዮጋት እሳቤ በመረዳት አዳብሩት፣ ተግብሩት፣ አበርቱን እያልን በአካባቢያችሁ ስለምታውቋቸው ደካማ ቤተ ክርስቲያኖች ከታች ለመንደርደሪያ ባቀረብነውና ይጠቅማል ያላችሁትን ጨምራችሁ መረጃውን በመነኩሴ መሳተፊያ መንገዶች ላኩልን። ይጠቅማሉ ብለን ያስቀመጥናቸው ዝርዝሮች ከታች በቀረቡት እንድትልኩልን በትህትና እናሳስባለን። 

 

  1. የቤተክርስቲያኑ ታቦት ስም

  2. የሚገኝበት አድራሻ/ኢትዮጵያ/ውጭ ሃገር 

    • ክልል/የቀድሞው ጠቅላይ ግዛት   

    • አውራጃ

    • ወረዳ/ዞንፍ

    • ከተማ/ገጠር

    • መለያ ቁጥር

  3. የተመሰረተበት ዘመን

  4. ርቀቱ  ከዋናው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት ጽህፈት ቤት፡ በኪሎሜትር/ማይል

  5. የትራንስፖርት አገልግሎት 

    • አስፋልት መንገድ

    • ኮረኮንች

    • የህዝብ መጉዋጉዣ

    • በከብት

    • አውሮፕላን

  6. የፈውስ ጸበል ቦታዎች

  7. የቤተክርስቲያኑ የቦታ ስፋት

  8. በዙሪያው ያሉ ዛፎች/ፍራፍሬዎችና ሌሎች ዕጽዋት

  9. የስልክ ቁጥር

  10. የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር

  11. ታቦቱ የሚነግስባቸው ወርና ቀን 

  12. ተጨማሪ የአገልግሎት ህንጻዎች

  13. የመብራት/ የውሃ /የመጸዳጃ ቤቶች/ስልክ

  14. ከሩቅ ለሚመጡ ምዕመናን በአካባቢው ያሉ ተፈላጊ አገልግሎቶች 

  15. ለሚመጡ ምዕመናን መረጃ የሚሰጡ የቤተክርስቲያኑ ወኪሎች ካሉ

  16. ቤተክርስቲያኑ የሚገኝበት ገላጭ ሰዕላዊ የፎቶ መረጃዎች

  17. ተጨማሪ ካለ መጨመር