ጥንተ እምነት

ጥንተ  እምነት

ጥንተ  እምነት

ገና አውሮፓውያንና ሌላው ዓለም ስለክርስቶስ ምንም ባላወቀበት ኢትዮጵያዊው ጃንደርባ  ለመሳለም ኢየሩሳሌም ሄዶ ሳለ፥ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሃፍ ሲያነብ መንፈስ ዕምነቱን ተመልክቶ፥ ሃዋርያው ፊሊጶስን በመላክ ገና በ34 ዓመተ ምህረት የክርስቶስን ማዳን አምኖ ፥ተጠምቆ ወደ ሃገሩ ክርስትናን ይዞ መመለሱ፡የሐዋርያት ሥራ ም፡ 8 ቁ 26፡39

·       ገና አውሮፓውያንና ሌላው ዓለም ስለክርስቶስ ምንም ባላወቀበት ኢትዮጵያዊው ጃንደርባ  ለመሳለም ኢየሩሳሌም ሄዶ ሳለ፥ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሃፍ ሲያነብ መንፈስ ዕምነቱን ተመልክቶ፥ ሃዋርያው ፊሊጶስን በመላክ ገና በ34 ዓመተ ምህረት የክርስቶስን ማዳን አምኖ ፥ተጠምቆ ወደ ሃገሩ ክርስትናን ይዞ መመለሱ፡የሐዋርያት ሥራ ም፡ 8 ቁ 26፡39

·       በ325 ዓመተ ምህረት በኒቅያ ንጉስ ቁስጠንጢኖስ በሰበሰባቸው  318 ሊቃውንት የጸደቀውን ትክክለኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በ328 ዓም በፍሬምናጦስ/አባ ሰላማ አማካይነት ከግብጽ ቅዱስ ማርቆስ መንበር በይፋ በመቀበል ጥንታዊ  ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስትሆን ታላቅ እምነት ያላቸው አባቶች ፣ ምዕመናንና ፣ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፡አፍርታለች።  /የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤት ክርስቲያን ሃይማኖት እምነትና ሥርዓት/ አቶ በእደ ማርያም እጅጉ ረታ 2004 ዓ ም/ LINK DOC

·       ዛሬ በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ፥ጌታ በተወለደበት በቤተልሄም፥ በተሰቀለበት ጎልጎታ፥ ሙት ባስነሳበት አልዓዛር፥ 40 ቀን ጾሞ በጸለየበት ቆርንቶስ እጠገብ በኢያሪኮ ባጠቃላይ 7 ገዳማት ይዞ መገኘት፣

·       በአክሱም የሙሴ ጽላት፡ በግሼን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል መገኘት፣

·       ዓለምን የሚያስገርመው የቅዱስ ላሊበላ ቤተክርስቲያናት፡ የበርካታ ቅዱሳን፡የያሬድ ማህሌት፡ የቅዳሴ ስርዓት፡ዝማሬ፡ መንፈሳዊ መጻህፍቶች፣ ታሪክና ቅርሷ ይመሰክራል።

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተችበት ጀምሮ በአማኞቿ  ጽናት በሃገር ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ስትታወቅ፣ በየጊዜው ዕድገትዋን የሚጎትቱ መሰረቷን ለማናጋት የሚችሉ ችግሮችም አልጠፉም።

More reading

 

Leave a comment

Comments

  • No comments found