People

ሆሳዕና በአርያም

 

 

 

      ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ ወደ ሚገኙት ወደ ቤተ ፋጌና..ወደ ቢታንያ በቀረበ ግዜ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ሄደው ምንም ያልተጫነባትን..የአህያ ውርንጭላ እንዲያመጡ ላካቸው በሉቃ.19-29 ጀምሮ እንደተፃፈው.. ባመጡም ግዜ በአህያዋ ላይ ተቀምጦ ሲሄድ..ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሊደርስ በተቃረበ ግዜ..የደብረ ዘይትን ተራራ ቁልቁል በመውረድ ላይ እያለ ሕዝቡ ሁሉ የዘንባባ ዝንጣሪ ወደ ምድር እያነጠፉ..ሆሳዕና በአርያም እያሉ ሲዘምሩ ፈሪሳዊያን ግን ኢየሱስን መምህር ሆይ ደቀመዛሙርትህን ዝም አሰኝ አሉት..ኢየሱስም እነሱ እንኳን ዝም ቢሉ እነኚ ድንጋዮች ይጮሐሉ ሲላቸው..የቤተ ፋጌ ድንጋዮች ሆሳዕና በአርያም በእግዚአብሄር ስም የሚመጣ ንጉስ የተባረከ ነው በማለት ይዘምሩ ጀመር..ጌታም በከፍተኛ አጀብና ዝማሬ እሱም ለተቀመጠባት አህያ እንኳን ሳይቀር ህዚቡ ሁሉ የለበሰውን ልብስና የዘንባባ ዝንጣፊ እያነጠፉ..በሆይታ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገባ ስለከተማዋም በጥፋት አብዝቶ አለቀሰላት..በኃላም ጌታ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ አንፅኦተ መቅደስ አደረገ..ያኔም የክርስቶስ ህማሙ ገባ..ለመሆኑ ሰሙነ ህማማት ማለት ምን ማለት ነው…የቃሉ ትርጓሜ ሰሙን ማለት ሳመንት ሲሆን..ህማማት ማለት ደግሞ “ሀመ ” ታመመ ሲሆን..ታመመ ማት በሽታ ያዘው ማለት ሳይሆን መከራን ተቀበለ ማለት ነው..ህማም መከራ ማለት ነው..ሰሙነ ህማማት ማለት ደግሞ የመከራዎች መከራ ሳምንት ማለት ነው..

 

ይሄም ከዛሬ ከእሁድ 6:00 ሰዓት እስከ አርብ ማታ ያለውን ያጠቃልላል..ይኼም የ5500 ዘምን ምሳሌ ነው..ከሆሳዕና ዕለት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ስቅለት ዓርብ 12:00 ሰዓት ድረስ ያለው አምስት ቀን ተኩል ይሆናል..ግማሿ ቀን የአምስት መቶ ዘመንን ስተወክል..አምስቱ ቀናት የአምስት-ሺ ዘመንን ይወክላሉ..በአጠቃላይ የአሽስት-ሺ አምስት መቶ ዘመን ምሳሌ ነው..እነኚ ቀናት እንደ ቤ/ክርስትያናችን ስርአት እንደ ዘመነ ኦሪት ይታሰባሉ..ስለእዚህ በእነዚህ ቀናት በቤ/ክ የሚሰጠው አገልግሎት..ገና ከባርነት እንዳልወጣን:ከመከራ እንዳልወጣን:በፍዳ ውስጥ እንዳለን አድርገን አስበን ስለሆነ አገለግሎቱን የምናከናውነው..ስርአቱ ሁሉ የብሉይ ኪዳን ነው..ስለእዚህም በእዚህ ሳምንት ውስጥ መስቀል መሳለምን ጨምሮ ሌሎች አብረውት የሚከለከሉ ስርአቶች አሉ..በእዚህ የመከራ ሳምንት ጌታችን ለሰው ልጆች ያለውን ፍጹም ሠላምና ፍቅር ግልጽ ያደረገበት..

 

እስከመቃብር ድረስ ወርዶ ለእኛ ያለውን ፍቅር ያሳየበት..በችንካር እንኳን ተቸንክሮ እያለ እጆቹን በፍቅር ዘርግቶ ከእቅፉ እንድንገባለት እየተለማመጠን እንዳፈቀረን ወደመቃብር የገባበትና ሞትን የገደለበት ሰሞን ነው..በእዚህ ሰሞን ካህናትና ምዕመናን በአፀደ ቤ/ክ ተሰብስበው..ከሐሜት ከአጥያትና ከነውር እርቀው ከረከሰውም ምግባር እራሳቸውን አቅበው..የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ህማም የሚያወሳውን ዜማ ሲያዜሙ..ግብረ ህማም በመባል የሚታወቀውን መጽሐፍ ሲያነቡና ሲሰሙ.ሲሰግዱና ሲፀልዩ ይሰነብታሉ..ካህናትና ምዕመናን በቤተ/ክ ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስሚል ደረስ ይሰግዳሉ..በተለይ ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ..ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ..ለ5500 ዘመን የሰውልጆች በጭለማ ግዞት ይኖሩበት እንደነበር ለመዘከር ነው..በሰሞነ ህማማት የጌታችንን ህማም ከማሰብ ጋራ በርካታ ህማሞችን የምናስብበት ግዜ ነው..ከሰኞ ጠዋት ጀምሮ በዕለት ዕለት በመከፋፈል..በየትኛው ቀን ምን ተደረገ ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እሞክራለው..በድጋሚ እንኳን ለሆሳዕና በዓል አደረሳችሁ ::

 

Source:

 

https://www.facebook.com/profile.php?id=100009301244360&fref=hovercard

 

Leave a comment

Comments

  • No comments found